CzeslawBassara

ቼስላው ባሳራ

ውድ ወንድሞቼ ሆይ፤

ወደ "ቃሉን ማወጅ" ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጣችሁ፤ በረከቶቻችሁ ልንሆን እንሻለን፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ በረከት ሆኖልናልና፡፡

የዚህ አገልግሎት ዓላማ የ"ቃሉን ማወጅ" ራእይ፤ ዘይቤ፤ ወይም ፕሮግራም ማስተማር አይደለም፡፡ ዓላማው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም ስለ መልእክቶቹ፤ ስለ መልእክቶቹ
መግለጫ እና አንቀጽ፤ መጽሐፍ ቅዱስን በተሻለ መንገድ መረዳትና ተግባራዊ ስለ ማድረግ ነው!

የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት በተረዳን መጠን አዲሱን ትውልድ ለክርስቶስ ለመማረክ የበለጠ እንንቀሳቀሳለን! ይህንን መልእክት በምትጠቀሙበት ጊዜ ስለዚህ አገልግሎት
እንድትጸልዩ አጥብቄ እጠይቃለሁ፡፡

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?



Results

Proclaiming the Word!

"ቃሉን ማወጅ" የዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አገልግሎት ክፍል ሲሆን የተቋቋመው ልጆችን በወንጌል ለመድረስ ነው፡፡ አገልግሎቱ በዓለም ዓቀፍ
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አገልግሎት ሥር በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ሠራተኞቹን መንፈሳዊ ፍላጎት ለማሟላት ይተጋል፡፡ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር
ቃል መሆኑን በእውነት ለሚያምኑ ሁሉ በረከት ነው፡፡

ይህ አገልግሎት "ቃሉን ማወጅ" ን በተለያዩ መድረኮችና ሁኔታዎች ይወክላል፡፡

ማስተማርና መስበክ

በልጆች የወንጌል ስርጭት ህብረት ተቋም ውስጥ በማስተማር፤
የልጆች የወንጌል ስርጭት ህብረትን መወከል፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆችና ሴሚናሪዎች ውስጥ በማስተማር፤
በኮንፈረንሶች፤ በጉዞ ቦታዎችና በቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ውስጥ በመናገር፤

የህጻናት የወንጌል ስርጭት ህብረትን ስለ መወከል፤
መጋቢዎችን እና የቤተክርስቲያን መሪዎችን በመጎብኘት፤
በዓለም ዓቀፍ መድረኮች፤ ምክክሮችና ኮንፈረንሶች ላይ በመወከል፤

መጻፍ፤
መረጃዎችና አነስተኛ ጽሑፎችን በመጻፍ፤ አብዛኛዎቹ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ፡፡
 
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡