ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

ሁለን ትተው ተከተሉት

ሉቃ 5፤1-11

ዕቅድ ቁጥር 1
እግዚአብሔር ሊያስተምርህ ዝግጁ ነው!

አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ጠይቅ አጠገብ ሳለ ህዝቡ በዙሪያው እያጨናነቁት የሚያስተምረውን የእግዚአብሔር ቃል ይሰሙ ነበር፤ (ሉቃ 5፤1)

ትምህርት ቁጥር 1
እኔ ለማዳመጥ ዝግጁ ከሆንኩ እግዚአብሔር ሊያስተምረኝ ዝግጁ ነው!
ዕቅድ ቁጥር 2
እግዚአብሔር ኃይሉን ሊያሳይህ ዝግጁ ነው!

በዚያን ጊዜ ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ዳርቻ ቆመው አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ወርደው መረባቸውን ያጥቡ ነበር፡፡ ከጀልባዎቹ መካከል የስምዖን
ወደ ነበረችው ገብቶ፣ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤ ከዚያም ጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር፤ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን፣
"ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ በልና ዓሣ ለማጥመድ መረባችሁን ጣሉ" አለው፡፡ ስምዖንም መልሶ "መምህር ሆይ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም፤
አንተ ካልክ ግን መረቦቹን እጥላለሁ" አለው፡፡ እንደዚያም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረባቸውም ይበጣጠስ ጀመር፡፡ በሌላ ጀልባ የነበሩት ባልንጀሮቻው
መጥተው እንዲያግዟቸው በምልክት ጠሯቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱን ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፣ ጀልባዎቹም መስጠም ጀመሩ፡፡ (ሉቃ 5፤2-7).
ትምህርት ቁጥር 2
ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ ዝግጁ ከሆንኩ እርሱ ኃይሉን ሊገልጥልኝ ዝግጁ ነው!

ዕቅድ ቁጥር 3
እግዚአብሔር ሊጠቀምብህ ዝግጁ ነው!

ስምዖን ጴጥሮስም ይህንን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ላይ ወድቆ፣ "ጌታ ሆይ እኔ ኃጥያተኛ ሰው ነኝና ከእኔ ተለይ" አለው፡፡ ይህንን ያለው እርሱና ከርሱ ጋር
የነበሩት በያዙት ዓሣ ብዛት ስለተደነቁ ነው፤ ደግሞም የስምዖን ባልጀሮች የነበሩት የዘብዴዎች ልጆች፣ ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ፡፡ ኢየሱስም ስምዖንን፣
"አትፍራ፤ከእንግዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ" እነርሱም ጀልባዎቹን ወደ ምድር ካስጠጉ በኋላ ሁሉን ትተው ተከተሉት፡፡ (ሉቃ 5፤8-11):

ትምህርት ቁጥር 3
እኔ ትሁት ለመሆን ዝግጁ ከሆንሁ፣እግዚአብሔር ሊጠቀምብኝ ዝግጁ ነው!

ከእግዚአብሔር የሆኑ ትምህርቶች:

ለማዳመጥ ዝግጁ ከሆንሁ፣ እግዚአብሔር ሊያስተምረኝ ዝግጁ ነው፤

ለመታዘዝ ዝግጁ ከሆንሁ፣ እግዚአብሔር ኃይሉን ሊያሳየኝ ዝግጁ ነው!

ትሁት ለመሆን ዝግጁ ከሆንሁ፣ እግዚአብሔር ሊጠቀምብኝ ዝግጁ ነው!


ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it , www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡