ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

ለማገልገል ድነናል!

የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይኖራል፡፡ የሚያገለግለኝም ቢኖር አባቴ ያከብረዋል፡፡ (ዮሐ12፤26)

አገልጋይ ጌታውን ይከተላል፤ የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ...

ጌታ ኢየሱስ አገልጋይ ጌታውን እንደሚከተል በግልጽ ተናግሯል! አለቃው ምን ማድረግ እንዳለበት የመንገር መብት በጭራሽ የአገልጋዩ አይደለም፡፡ ክርስቶስን መከተል
ማለት በርሱ መንፈስ መመራት፤በርሱ ጥበብ ምርጫዎቸን ማድረግ፤ለርሱ መኖር፤እርሱ እንድናደርግ የሚፈልገውን ሁሉ ማድረግ ማለት ነው!

አገልጋይ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን በግሪክ ዶሎስ (ከጌታው ጨርሶ የማይለይ ባሪያ) የሚለውን ያመለክታል፡፡ አንዳንዴ ዴአኮኖስ (ዲያቆን ወይም አገልጋይ)
የሚለውን ያመለክታል፡፡ ዶሎስ እና ዴአኮኖስ ተመሳሳይ ቃላት በመሆናቸው ይሄ ትክክል ነው፡፡ ሁለቱም ቃላት በራሱ ፈቃድ እንደወደደ የማይኖረውን፤ ነገር ግን
በዋጋ የተገዛ የጌታው ንብረት የሆነን ሰው ያመለክታሉ፡፡ እኛ የጌታን ፈቃድ ለማገልገል በዋጋ የተገዛን ነን፡፡

አገልጋዮቹ እንዲሰሩት ጌታ ኢየሱስ ያዘጋጀው ሥራ ምንድነው? ምንም እንኳ ዋጋ የሚያስከፍልና ክብርን የሚነካ ቢሆንም አብረዋቸው ለሚያገለግሉት እንደባሪያ
እንዲሆኑና እነርሱን ለማገዝ ሲባል ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፈቃደኛ በመሆን እንዴት ሊያገለግሉት እንደሚገባ ነግሮአቸዋል፡፡

አገልጋዮቹ ኢየሱስ ባለበት ሥፍራ ሁሉ አሉ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይኖራል፡፡ 

አባቴ ከጥንት ጀምሮ ይሰራል፤ እኔም ደግሞ እሰራለሁ፤ (ዮሐ 5፤17) እኛ ፍጥረቱ ነንና እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካም ሥራ
ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን (ኤፌ 2፤10)

በዓለማችን ውስጥ እግዚአብሔር በሥራ ላይ ነው፡፡ እርሱ እየሰራ ባለው ሥራ ውስጥ መሳተፍ እንችላለን፤ እንሳተፍማለን፡፡ አገልግሎት ለመጋቢዎች ወይም የስነ-መለኮት
ትምህርት ለተማሩት ብቻ አይደለም፡፡ በእነዚህ ሰዎች ላይ ብቻ የምንደገፍ ከሆነ የምንፈጽመው እጅግ በጣም ጥቂት ብቻ ይሆናል፡፡
አገልጋዮች በእግዚአብሔር ይከብራሉ፤... የሚያገለግለኝም ቢኖር አባቴ ያከብረዋል፡፡
 
እግዚአብሔርን በደስታ፣በሐሴት እና በመሰጠት ስናገለግል እግዚአብሔር ያከብረናል፤ ከዚህ ክብር ጋር ሊስተካከል የሚችል ምድራዊ ክብር የለም፡፡ የሚያገለግሉት
በእግዚአብሔር ይከበራሉ፡፡ ታላቁ የቫዮሊን ተጫዋች ፓጋኒኒ ድንቅ የሆነችውን ቫዮሊኑን መጫወት በማትችልበት ሁኔታ ለጀነዋ ከተማ ለመስጠት ተናዘዘ፡፡ የዚህ አይነት
መሳሪያ ጥቅም ላይ ከዋለና በአግባቡ ከተያዘ የእንጨቱ መበላሸት በእጅጉ አነስተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ሥራ ላይ ካልዋለ መበስበስ ይጀምራል፡፡ የፓጋኒኒ ውብ ቫዮሊኑንም
በአሁኑ ወቅት ለቅርስነት ካልሆነ በቀር በትል ተበልታና ከጥቅም ውጭ ሆና ትገኛለች፡፡ የክርስቲያንም ለማገልገል ፈቃደኛ አለመሆን እንዲሁ ጠቃሚ የመሆን አቅሙን ያበላሽበታል፡፡

አገልጋዮች ጌታን ይከተላሉ! አገልጋዮች ኢየሱስ ባለበት ሥፍራ ይገኛሉ! አገልጋዮች በእግዚአብሔር ይከብራሉ!

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡