ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

በሸክላ ሰሪው ቤት ውስጥ

ኤር18፤ 1-11

የጽሑፉ ታሪካዊ ትርጉም


ሸክላ ሰሪው ግልጽ እቅድ እንደነበረው ኤርሚያስ አስተዋለ፡፡ ሸክላ ሰሪው ለሸክላው ልዩ ቅርጽ ለመስጠት የተካኑ እጆቹንና የተለያዩ መሳሪያዎችን ተጠቀመ፡፡
ሸክላው የሚያገለግለው በሸክላ ሰሪው አዕምሮ ውስጥ የነበረን ሐሳብ ነው፡፡
 • ሸክላ ሰሪው ጭቃውን መረጠ እንጂ ጭቃው ሸክላ ሰሪውን አልመረጠም፤
 • ሸክላ ሰሪው የወደደውን ጭቃ መረጠ፡፡
 • ሸክላ ሰሪው ለሸክላው ቅርጽ ለመስጠት ጉልበቱን ተጠቅሟል፡፡
ትልቁ ሸክላ ሰሪ ለእያንዳንዳችን ዕቅድ አለው፡፡ (ኤር 1፤18; 2፤11)
 • ኤርሚያስ እግዚአብሔርን እንደ ሸክላ ሰሪ እና እስራኤልን እንደ ጭቃ ተመለከተ፡፡
 • እግዚአብሔር ለእስራኤል እቅድ ነበረው፡፡
 • እግዚአብሔር የተለያዩ በረከቶችን በመላክ ልዩ የሆነ ቅርጽን ሰጣት፤
 • እግዚአብሔር ፍርድን በመስጠት ልዩ የሆነ ቅርጽን ሰጣት፤

የጽሑፉ መንፈሳዊ ትርጉም፤


1. ሸክላ ሰሪው ጭቃውን አገኘ፤

 • መዝ 40፤ 2-3.
 • ለሌሎች ቆሻሻ ጭቃ ብቻ ነበርን፤ እግዚአብሔር ግን ሸክላን አየ፡፡
 • እግዚአብሔርን እኛ አልመረጥነውም ግን እግዚአብሔር እኛን መረጠን፤
 • 1ቆሮ 6፤ 9-11
 2. ሸክላ ሰሪው ለሸክላው የመጀመሪያውን ቅርጽ ለመስጠት አፈሩን ከውሃ ጋር  ቀላቀለው፤ 
 • ኤፌ 5፤26
 • ገላ 4፤19
 • ፊል 3፤10
 • ሮሜ 8፤ 29፣ 12፤2
3. ሸክላ ሰሪው ለመደፊት ሸክላው እንዲሰበር ሊያደርጉ የሚችሉ በጭቃው ውስጥ የነበሩትን ጥቃቅን የአየር እንክብሎችን ለማስወጣት እግሮቹን ተጠቀመ፡፡ 
 • ኤፌ1,20-22
 • "የሚያፈሱ" ክርስቲያኖች፤
 4. የመጨረሻውን ቅርጽ ለማውጣት ሸክላ ሰሪው ሸክላውን በማንኮራኩር ላይ አደረገው፤
 • በማንኮራኩር ላይ አሽከረከረው፤
 • አስፈላጊ እስከሆነ ጊዜ ድረስ በማንኮራኩር ላይ አቆየው፤
 • ሸክላ ሰሪው እስከመጨረሻው ድረስ አንዳንድ ባዕድ ነገሮችን ከሸክላው ላይ ለማስወገድ ጣቶቹን ይጠቀም ነበር፤ (1 ጴጥ5፤ 6).
 5. ሸክላ ሰሪው ሸክላውን ለማድረቅ የጸሐይ ብርሃንን ተጠቀመ፤
ይህ ክንውን እጅግ በጣም አስፈላጊ ቢሆንም የመጨረሻና አጥጋቢ አይደለም፤ሸክላ ሰሪው እዚህ ላይ ቢያቆም ሸክላው ለረጅም ጊዜ ሊያገለግል አይችልም፡፡ የሸክላ ሰሪው ዓላማ ከዚህ አልፎና ጠልቆ ይሄዳል፡፡

6. ሸክላ ሰሪው ሸክላውን በእቶን እሳት ውስጥ ማስቀመጥ ይኖርበታል፤

 • ሀ) እሳቱ ቆሻሻውን ሁሉ ያስወግዳል፤
 • ለ) ከዚህ ሂደት በኋላ ሸክላው እጅግ ጠንካራ ይሆናል፤
 • ሐ) 1 ጴጥ 4፤12-14
7. ሸክላ ሰሪው እቃውን አስዋበ፤ 
ሸክላው ጥሩ ብቻ ሳይሆን ለዓይን የሚስብ መሆን አለበት፤ (ሮሜ 12፤ 2)

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡