ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

በተስፋ መቁረጥ ወቅት የእግዚአብሔር ማበረታታት ያስፈልገናል፤

ዕብ 10፤23-35 - የእግዚአብሔር ህዝቦች ሁሉ መበረታታትን ይፈልጋሉ፤

1. ይስሃቅ ማበረታታት አስፈልጎት ነበር፤ 'በረሃብ ሀገር እባርክሃለሁ!'
"እግዚአብሔር ለይስሃቅ ተገልጦ እንዲህ አለ፤እኔ በምነግርህ ምድር ተቀመጥ እንጂ፣ ወደ ግብጽ አትውረድ፤ ለጥቂት ጊዜ እዚሁ ተቀመጥ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤
እባርክሃለሁ፤ ይህንን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘርህ በመስጠት ለአባትህ አብርሃም በመሃላ ገባሁትን ቃል አጸናለሁ" (ዘፍ 26፤2-3)

(ዘፍ 26፤12-13).

ይስሃቅ ይኖር በነበረበት ሀገር የምግብ እጥረት ባጋጠመው ጊዜ እግዚአብሔር ወደ ግብጽ እንዳይወርድ ነገር ግን ባለበት ሀገር እንዲቆይ ተናገረው፡፡ እግዚአብሔርም
በዚህ አገር እንደሚባርከው ለይስሃቅ ቃል ገባለት፤

እግዚአብሔርም ይስሃቅን አበለጸገው፡፡ በዘራም ጊዜ መቶ እጥፍ ምርትን ሰበሰበ፡፡ ይስሃቅ እጅግ ባለጠጋ እስኪሆን ድረስ ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረለት ሄደ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ትግል፣ዕጥረትና ጉዳት ባጋጠመን ሥፍራ እግዚአብሔር ሊባርከን ይችላል፡፡ ምናልባት ህመምና ስጋት ካገኘን ሥፍራ ለማምለጥ እንዳዳ ይሆናል፡፡
እግዚአብሔር ብርቱ ኃይሉን ስለ እኛ በመግለጥ እጥረትና ሥጋት ባጋጠመን ሥፍራ ሊባርከን ቃል ገብቷል፡፡

2. ራሄል: '...እግዚአብሔርም ራሄልን አሰባት!'


እግዚአብሔርም ራሄልን አሰባት፤ልመናዋንም ሰምቶ ማህጸንዋን ከፈተላት (ዘፍ 30፤22)

ራሄል ለረጅም ወቅት መካን ነበረች፤ እግዚአብሔርም የረሳት መሰለ፡፡ ሌሎቹ ልጆች በልጆች ላይ ያገኙ ነበር፡፡ ራሔል ብቻ ከእግዚአብሔር በረከት ውጭ የሆነች
መሰለ፡፡ እግዚአብሔር የረሳት በመሰለ ጊዜ ግን መጽሐፍ እንደሚናገር 'እግዚአብሔር ራሄልን አሰበ'! ራሄል አልተረሳችም! እግዚአብሔር አሰባት፤ለቅሶዋንም ሰማ፡፡
እርሱም ነቀፌታዋን አስወግዶ ወንድ ልጅን ሰጣት፡፡ እርሷም ዮሴፍ ስትል ስም አወጣችለት፡፡ የራሄል ልጅ ዮሴፍ ከሌሎች ልጆች ሁሉ በላይ ከፍ ተደረገ፡፡

ዮሴፍ ከፊቱ ብሩህ ተስፋ ነበረው፤ እናም የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ፡፡ ምንም እንኳ ራሄል በረከቷን ለማግኘት ረጅም ጊዜ መጠበቅ የነበረባት ቢሆንም በመጣ
ጊዜ ግን ልዩ እና ሌሎችን ሁሉ የሚያስንቅ ነበር፡፡

አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ሌሎች በረከትን በበረከት ላይ ሲያገኙ፣ እግዚአብሔር እኛን የረሳን ሊመስለን ይችላል፡፡ ራሄን ያሰበ እግዚአብሔር በርግጠኛነት እኛንም ያስበናል፤እጅግ ልዩና ለቆይታችን የሚመጥን በረከትን ይባርከናል፡፡
በፍጹም ተስፋ መቁረጥ የለብንም፤ ነገር ግን በተስፋ እና በጽናት ልዩ የሆነውንና እግዚአብሔር ያዘጋጀልንን በረከት ለመቀበል መጠበቅ አለብን፡፡

3. ያዕቆብ: 'ላባ ባንተ ላይ የሚያደርገውን ድርጊት ሁሉ አይቻላሁ፤'


... 'ላባ ባንተ ላይ የሚያደርገውን ድርጊት ሁሉ አይቻላሁ፤' (ዘፍ 31፤12)

ዘፍ 31፤12.6.7.41

ያዕቆብ በላባ ሥር ለ20 ዓመታት ሲንገላታ ላባን ትቶ ወደ አባቶቹ ቤት እንዲሄድ እግዚአብሔር ተናገረው፡፡ እግዚአብሔርም ለያዕቆብ 'ላባ ባንተ ላይ የሚያደርገውን
ድርጊት ሁሉ አይቻላሁ' አለው፡፡ እግዚአብሔር ያዕቆብን ከላባ እጅ ነጻ አወጣው፡፡ ምንም እንኳ ያዕቆብ በላባ ሥር ለረጅም ጊዜያት ሲንገላታና ሲታለል ቢኖርም
ከእግዚአብሔር የተሰወረ አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር በያዕቆብ ላይ ሲፈጸም የነበረውን ኢፍትሃዊ ድርጊቶችና ጭቆናን ሁሉ ይመለከት ነበር፤ እናም እግዚአብሔር
ጣልቃ የሚገባበትና ነጻ የሚያወጣበት ሰዓት ደረሰ፡፡

በህይወታችን የምናልፍበትን የህመምና የሥቃይ አጋጣሚዎች ሁሉ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እግዚአብሔር የምናልፍባቸውን መከራዎች አያውቅም ብለን በማሰብ
ተስፋ መቁረጥ የለብንም፤፡

እግዚአብሔር የምናልፍባቸውን ኢፍትሃዊ ነገሮችና እንግልቶችን ሁሉ ያውቃል፤ ጣልቃም በመግባት ከጨቋኞቻችንና ከክፉ አድራጊዎችን እጅ ነጻ ያወጣናል፡፡

4. ኤሊያስ: 'ገና የምትሔድበት ብዙ መንገድ በፊትህ አለ!'


በምድረባም ውስጥ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዘ፤ ወደ አንድ ክትክታ ዛፍ እንደመጣም ከሥሩ ተቀምጦ ይሞት ዘንድ 'እግዚአብሔር ሆይ በቅቶኛል፤ እኔ ከቀደሙት
አባቶች አልበልጥምና ነፍሴን ውሰዳት' ብሎ ጸለየ፤...የእግዚአብሔርም መልአክ እንደገና ነካ አደረገው 'ሩቅ መንገድ ስለምትሄድ ተነስትህ ብላ' አለው፡፡

(1ነገስት 19፤4.7).

1ነገ 19፤1-7፣ 15-16; 2 ነገ 2, 1.11

የኤሊያስ ህይወት ከኤልዛቤል ዛቻ የተነሳ አደጋ ላይ በወደቀ ጊዜ ተስፋ በመቁረጥ ይሞት ጸለየ፡፡ ለእግዚአብሔርም 'በቃ ልሙት'አለ፡፡ ከመኖር ይልቅ መሞት
እንደሚሻልም ተሰማው፡፡ ለህይወቱ ምንም ዓይነት ዓላማን ማየት አልቻለም፡፡ እግዚአብሔር ገና በእርሱ ሥራ እንዳለው መገንዘብ አልቻለም፡፡ እግዚአብሔር
መልአኩን ልኮ አበረታታው፡፡ ገና የሚጓዘው ረጅም መንገድ እንዳለውም ነገረው፡፡ እርሱ እንዲፈጽመው እግዚአብሔር ያስቀመጠለት ብዙ ጠቃሚ ሥራዎች ገና
አሉ፡፡ ለሁለት ህዝቦች ነገስታት መቀባት ነበረበት፤ እንዲሁም ተተኪውን ኤልሳን መቀባት ነበረበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኤሊያስ ሞትን እንዳያይና በእሳት ሰረገላ ወደ
ሰማይ በህይወት እያለ እንዲወጣ የእግዚአብሔር እቅድ ነበር፡፡ ፡፡ ኤሊያስ ከነበረበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት የተነሳ እግዚአብሔር ለህይወቱ ያለውን ድንቅ ዓላማ
ሊገነዘብ አልቻለም፡፡

በምትኩ ይሞት ዘንድ ጸለየ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አበረታታው፤የህይወቱን ዓላማና ተግባር ይፈጽም ዘንድ አገዘው፡፡ በህይወታችን ውስጥ በከባድ ሸክሞች ምክንያት
ከጊዜ ወደ ጊዜ ተስፋ እንቆርጣለን፤ እናም እግዚአብሔር ይወስደን ዘንድ፤ የዚህ ዓለም ነገር በቀኝ በማለት እንጸልያለን፡፡ ገና የምንጓዘው ረጅም መንገድ እንደቀረንና
እግዚአብሔር ገና ብዙ ሥራ ለእኛ እንዳለው አናስተውልም፡፡

እግዚአብሔር እንድንሄድና በእርሱ መንግስት እንፈጽም ዘንድ የሰጠንን ሁሉንም ሥራዎች እንድንፈጽም ሊያበረታታን ይፈልጋል ፡፡

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡