ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

በቶሎ እመጣለሁ! ጌታ ኢየሱስ

ራዕ 3፤ 11-12

1. 'እነሆ ቶሎ እመጣለሁ!'

1.1. የጌታ ኢየሱስ ወደ ኤፌሶን፤ ጴርጋሞን እና ሰርመኔስ መምጣት ለፍርድ ሲሆን ወደ ፍላድልፍያ የመጣው ግን የመከራቸውን ዘመን ለመዝጋት ነበር፡፡

1.2. 'እነሆ በቶሎ እመጣለሁ!' ለጨቋኞች ማስጠንቀቂያ ሲሆን ለጭቁኖች ደግሞ ማበረታቻ ነው፡፡
 
1.3. ክርስቲያኖች ለጌታ ኢየሱስ ምጽዓት ሁሌም ዝግጁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ (ራዕ፤3፤3) የኢየሱስ ክርስቶስ በድንገት መምጣት በታማኝነት እያገለገሉ ለመጠበቅ አነሳሽ ነው፡፡

2. ቤተ መቅደሱ


በራዕ 3፡10 የተጠቀሰው የመጠበቅ ሰዓት በዚህ ሥፍራ የተገለጸው ከጌታ ኢየሱስ ለቤተክርስቲያኑ መመለስ ጋር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ የሚዛመደው አንድም ከሚሊኒየሙ
መንግስት አሊያም ከአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ጋር ነው፡፡ እውነተኛ አማኝ በእግዚአብሔር ፊት የአገልግሎትና የክብር ሥፍራ ይሰጠዋል፡፡

3. ስሞቹ


የስሙ ሶስት ጊዜ መጠቀስ በጌታ ኢየሱስ ላለው የዘላለም ደህንነት ዋስትናን ይሰጣል፡፡
  • የአምላኬ ስም ባለቤትነትን ያሳያል፤
  • የከተማዋ ስም ሰማያዊ ዜግነትን ያሳያል፡፡
  • እንዲሁም አዲሱ ስሜ ከጌታ ኢየሱስ ጋር ወራሽ መሆኔን ያሳያል፡፡
4. ዘውዱ

4.1. ለአሸናፊዎች የተዘጋጀው ዘውድ፤
ለአሸናፊዎች የተዘጋጀው 'ዘውድ' በሩጫ ውድድር ላሸነፉ የሚሰጥ አክሊል ነው፡፡ ይህ ሽልማት በስፖርት ውድድሮች በምትታወቅ ከተማ የተለመደ ሲሆን በአዲስ
ኪዳን ደግሞ ታማኝ አገልግሎትን ለመሸለም የተለመደ ምልክት ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህንኑ ከመሞቱ ጥቂት ቀናት በፊት ለጢሞቲዎስ ጻፈለት፡፡ 2 ጢሞ 4፤ 7-8.

4.2. ዘውድን ማጣት
አንድ ሰው በስነ ምግባር ጉድለት አግኝቶ የነበረውን ዘውድ ሊያጣ ይችላል፡፡ (2 ዮሐ 8) ዘውዱ ከጌታ ኢየሱስ ጋር አብሮ ወራሾች ለሆኑ አሸናፊዎች የገዢነት
ሥልጣን ማሳያ ነው፡፡ የክርስቶስ የፍርድ ወንበር የሽልማት ወይም የሐዘን ጊዜ ነው፡፡ (2 ቆሮ 5፤ 10)

5. አምዶቹ /ምሰሶዎች/
አሸናፊዎች በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አምድ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡ አምዶች /ምሰሶዎች/ የማይናወጡና የማይነቃነቁ የአንድ ህንጻ ክፍሎች ናቸው፡፡
በቤተመቅደስ ውስጥ ምሰሶ መሆን በክርስቶስ መንግስት ውስጥ ዋንኛ የአገልግሎት ሥፍራን ያመለክታል፡፡ (የሚከተሉትን ተመልከት: ኢሳ. 22, 23; ሉቃ 19, 16-19).

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡