በወንጌል ተልዕኮዎች ውስጥ የምንሳተፈው ለምንድነው
ማቴ 28፤18-20;
ማር 16፤15;
ዮሐ 20፤21;
ሮሜ 10፤13-15;
የሐዋ. ሥራ 13፤2-4
ያለወንጌል የሆኑት ህዝቦች ወንጌል እንዲሰበክ ከፈቀዱት ይልቅ በብዙ ድህነት፤ ወንጀል፤ በሽታ፤ የፈረሱ ቤተሰቦች፤ ዲቃላ ልጆች፤ ስስት፤ሙስና እና ጦርነት መጠቃታቸው
ታሪካዊ እውነት ነው፡፡
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ6000 ዓመታት ውስጥ 14,530 ጦርነቶች ተካሄደዋል፡፡ ይህ በአማካይ 2.6 ጦርነቶች በየዓመቱ እንደ ማለት ነው፡፡ አንድ የጠላት ወታደር
ለመግደል ቄሳርን $.75 አስወጥቶት ነበር፡፡ ናፖሊዮንን ደግሞ $3,000፤ በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት አንድን የጠላት ወታደር ለመግደል $21,000 ወጥቷል፡፡
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ደግሞ $200,000 ነበር፡፡
ዘመናዊው ጦርነት ደግሞ $1,000,000 በነፍስ ወከፍ ያስወጣል፡፡
ይህንን ያህል ገንዘብ በወንጌል ተልዕኮ ላይ ቢውል እስኪ አስቡ!
የወንጌል ተልዕኮ ምክንያቶቻችን፡-
1. የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ታላቁን ተልዕኮ ለመፈጸም፤ (ማቴ 28፤19-20)
ሀ. ለህንጻዎቻችን የበለጠ ትኩረት መስጠት ጀምረናል፤
ለ. በቁጥር ብዛት ላይ የበለጠ ትኩረት አድርገናል፤
ሐ. ባለን ዝና ተይዘናል፤ (ምን ያህል ባለሙያዎች አሉን?)
2. የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ርህራሄ ለማካፈል፤ (ማቴ 9፤36-38; 18፤10-14).
ሀ. ከላይ የሆነ ጩሐት መስማት አለብን፤ ('ወደ ቆርኔሊዎስ ቤት ሂድ!')
ለ. ከታች የሆነ ጩሐት መስማት አለብን፤ ('ወደ ወንድሞቼ አንድ ሰው ላክ!')
ሐ. ከውጭ የሚሰማውን የጩሐት ድምጽ መስማት አለብን፤ ('ወደ መቄዶኒያ ና!')
3. ሰዎችን ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማምጣት እግዚአብሔር ለማክበር፤ (ዮሐ3፤16; የሐዋ. ሥራ 1፤8, ሮሜ10፤13-15)
ሀ. ከተስፋ መቁረጥና ከባዶነት ልጆችን እንዲድኑ ማድረግ፤
ለ. እስረኞችን በእስር ቤታቸው ውስጥ እንዲድኑ ማድረግ፤
ሐ. በየአካባቢው ያሉ ሰዎችን በመጎብኘት እንዲድኑ ማድረግ፤
መ. በወንጌል ተልዕኮ በዓለም ዙሪያ ያሉ ነፍሳት እንዲድኑ ማድረግ፤
4. የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አካል መገንባት፤ (ኤፌሶን 4፤12-16).
ሀ. አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለወንጌል የሚላኩ ሰዎች ምንጭ ናት፤
ለ. አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለወንጌል ተልዕኮ የጸሎት ማዕከል ነች፤
ሐ. አጥቢያ ቤተክርስቲያን የወንጌል ተልዕኮ መልዕክተኞችን የምትሰጥ ናት፤
ዶ/ር ቼስላው ባሳራ
This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
; www.proword.eu