ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

በጌታ ኢየሱስ እግር ሥር

1. የኃጥያት ይቅርታ - ሉቃ 7፤38
ፈሪሳዊው ጌታ ኢየሱስን በቤቱ ቢጋብዘውም በእግሩ ስር በጭራሽ አልተቀመጠም ነበር፡፡ ይልቁኑ ከእርሱ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጥን ወደደ፡፡ ሴትየዋ ግን ኢየሱስን በቤቷ
አልጋበዘችውም ነበር፡፡ /ምናልባትም ቤት የላትም ይሆናል፡፡/ ነገር ግን ትልቁን ችግሯን ታውቅ ነበር፡፡ እርሱም ኃጥያቷን! የኃጥያት ይቅርታም እንደሚያስፈልጋት አውቃ ነበር፡፡
እናም ኃጥያቷን በጌታ ኢየሱስ እግር ሥር አኖረች፡፡
ጌታ ኢየሱስ ኃጥያትን ይቅር የሚል አምላክ ነው!

2. ትክክለኛ አስተምህሮ - ሉቃ 10፤39
ማሪያም መማር እንደሚያስፈልጋት ታውቅ ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስን ወደ ቤታቸው ወደ ቢታኒያ የጋበዘችው ማርታ ነበረች፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ እግር ሥር የተቀመጠችው ማሪያም
ነበረች፡፡ መማር ትኩረትን ይጠይቃል፡፡ እርግጥ ነው ጌታ ኢየሱስን የጋበዘችው ማሪያም አይደለችም፡፡ ነገር ግን ከሁሉ የተሻለውን ሥፍራ ማለትም በጌታ ኢየሱስ እግር ሥር መሆንን
መረጠች፡፡ እርሱም "የተሻለ ድርሻ" ነበር፡፡ /ሉቃ10፡42/
ጌታ ኢየሱስ እውነት የሆነ፤ የሚያውቀንና የሚወደን አምላክ ነው!

3. መጽናናት፤ - ዮሐ11፤32

ማሪያም የወንድሟ የአልዓዛር ሞት ደረሰባት፡፡ ምንም እንኳ አይሁዳውያን ወደ መቃብሩ ስፍራ ትሄዳለች ብለው ቢገምቱም ትኩረቷን የወሰደው ግን የመቃብሩ
ስፍራ አልነበረም፡፡ የተለያየ ችግር ካለባቸው ሰዎችም ብዙ መጽናናትን እንደማታገኝ ተረድታ ነበር፡፡ ማርያም ትክክለኛውን ሥፍራ ማለትም በጌታ ኢየሱስ እግር
ሥር መሆንን መረጠች፡፡ እርሱ ብቻ መጽናናትን ማምጣት ይችላልና፡፡ በለቅሶና በሀዘን ፈንታ ኢየሱስ ለማሪያም ልብ ደስታን ሰጠ፡፡
ጌታ ኢየሱስ በችግሮቻችን ወቅት የሚጠነቀቅልን አምላክ ነው!

4. የህጻኑ ህይወት፤ - ሉቃ 8፡41
የህጻኑ መሞት ኢያኢሮስን ወደ ኢየሱስ እንዲመለከት አደረገው፡፡ ፈልጎ ባገኘውም ጊዜ በእግሩ ስር ወደቀ፡፡ ለህጻኑ ከኢየሱስ በቀር ማንም ህይወትን ሊሰጥ እንደማይችል
ተረዳ፡፡ ኢያኢሮስም ህጻናት ያለጌታ ኢየሱስ ሟች የመሆናቸውን እውነት አረጋገጠ፡፡ ህጻናት ከወላጆች ፍቅር፤ ከሚተነፍሱት አየር፤ ከሚኖሩበት ቤት፤ ከልብስና ከምግብ ይልቅ
ጌታ ኢየሱስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ኢያኢሮስ ከሞተችው ህጻኑ ችግር ጋር ወዴት መሄድ እንዳለበት አውቋል፡፡
ጌታ ኢየሱስ ለህጻናት ህይወትን መስጠት የሚወድ አምላክ ነው፡፡

5. ምስጋና፤ - ሉቃ 17፡16
አስሩ ለምጻሞች ጌታ ኢየሱስን አገኙትና ሁላቸውም የእግዚአብሔርን ፍቅር ተቀበሉ፡፡ ሁላቸውም ከነበረባቸው የለምጽ ደዌ ነጹ፡፡ ወደ ቀደመው ጤናማ ህይወታቸውም
ተመለሱ፡፡ ነገር ግን ከመካከላቸው ምስጋናን ለማን ማቅረብ እንዳለበት የተገነዘበው ሳምራዊው ብቻ ነበር፡፡ እርሱም ተመልሶ በጌታ ኢየሱስ እግር ሥር ወደቀ፡፡ አስገራሚው ነገር
የአንዱ መመለስ ሳይሆን የቀሩት ዘጠኙ አለመመለስ ነው፡፡ ሳምራዊው ሁለት ተሐድሶን አገኘ፡፡ ሥጋዊና መንፈሳዊ! ምስጋናን ማቅረቡ መንፈሳዊነቱን ያመለክታል፡፡
ጌታ ኢየሱስ ምስጋናችን የሚገባው አምላክ ነው፡፡

6. ድል በፍርሃት ላይ፤ - ራዕ 1፤17
ሐዋሪያው ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስን በክብሩ ሲያየው ፍርሃት ወደቀበት፡፡ ጌታ ኢየሱስን ያውቀው ነበር፤ አብሮትም ተራምዶ ነበር፤ ሲያስተምርም ሰምቶ ነበር፤ ዳስሶትም ነበር፤ በክብሩ
ባየው ጊዜ ግን ምንም በእድሜ የገፋ ቢሆንም በእግሩ ስር ወደቀ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያና መጨረሻ መሆኑንም በሚገባ ተረደ፡፡ ኢየሱስ ይናገር ዘንድ በፊቱ ጸጥ አለ፡፡ ሐዋሪያው
ዮሐንስ ለጌታ ኢየሱስ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ምሳሌ ነው፡፡ በዓለም ምርጡ ቦታም በጌታ ኢየሱስ እግር ሥር መሆኑን ተረድቷል!
ጌታ ኢየሱስ ሙሉ ህይወታችንና ክብራችን የሚገባው አምላክ ነው፡፡

Dr. Czeslaw Bassara

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡