ቼስላው ባሳራ
በ1948 በፖላንድ ሀገር ብዜስቲ በምትባል ኦስዊዝም አጠገብ በምትገኝ ከተማ በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ተወለዱ፡፡
በ1965 ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸው ተቀበሉ፡፡ በዚሁ ዓመት የልጆች አገልግሎትን በፖላንድ ጀመሩ፡፡ እስከ 1969 ድረስ በትምህርትና በሥራ ላይ
በመሆን በኦስዊዝም አካባቢ ቆዩ፡፡
ከ1969 - 1974 ፖላንድ ዋርሶ ከተማ በሚገኘው የክርስቲያን ስነመለኮት አካዳሚ ውስጥ የስነመለኮት ትምህረት አጠኑ፡፡
በ1972 ከኤሌና ጋር ጋብቻ መሰረቱ፡፡ ሁለት ልጆችንም አፈሩ፡፡ ቦግዳን (በ1975 ተወለደ፡፡) እና ዶሮታ (በ1979 ተወለደ፡፡)፡፡ ሁለቱም ያገቡ ሲሆን
ከሚስቶቻቸው (አግኒስካ እና ኮንራድ) ጋር ልጆችን በወንጌል የመድረስ ህብረት (ልወመህ) ውስጥ ያገለግላሉ፡፡
በ1975 በፖላንድ ሀገር ውስጥ የማስተርስ ዲግሪውን በስነመለኮት ትምህርት አገኙ፡፡
በ1976 የልወመህን የመሪዎች ሥልጠና ተቋም በኪልችዝመር ሲውዘርላንድ ውስጥ አጠናቀቁ፡፡
ከ1969 - 1990 ለልጆችና ለወጣቶች የሚሆን የወንጌል ሥርጭት አደራጁ፤ እንዲሁም አስተማሪዎችና ቤተሰብን አሰለጠኑ፡፡
ከ1982 - 1990 ቤተክርስቲያን በመትከል እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትቤቶችና በቤተክርስቲያናት ውሰጥ በማስተማር በፖላንድ አገለገሉ፡፡
ከ1991 እስከ 2006/2007 ከባለቤታቸው ከኤሌና ጋር በመሆን የመካከለኛውና የምስራቅ አውሮፓ ልወመህ ዳይሬክተር በመሆን አገለገሉ፡፡ በራሺያና
በመካከለኛው ኤሲያ ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ እንዲሁም በ30 ሀገሮች ለብሔራዊ መሪዎች መመሪያ በመስጠት አገለገሉ፡፡ የአውሮፓ ፊልድ ካውንስል አባል
በመሆንም አገልግለዋል፡፡
ከ2000 - 2006 ቤልጅየም ሄቨርሊ/ሊዩቨን በሚገኘው የኢቫንጀሊካል ፋኩልቲ ውስጥ የስነመለኮት ትምህርትን በዶክተሬት ደረጃ አጠኑ፡፡
በ2006 በሲስተማቲክ ቲዎሎጂ፤በ 'ፖስት ሞደርን ሄርሜነቲክስ እና ኢቫንጀለስቲክ ሪሰፖንስ' የዶክተሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡
በ2008 'ቃሉን ማወጅ!' ማለትም የልወመህ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አገልግሎት ጀመሩ፡፡
ዶ/ር ቼስላው ባሳራ እንግሊዘኛ፤ ጀርመኒኛ፤ ራሽያ፤ ፖሊሽ እና ኢስፔራንቶ ቋንቋዎችን ይናገራሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አገልግሎታቸው በሁሉም አህጉራት
ከ60 ሀገሮች በላይ ተዳርሷል፡፡
"በቀረውስ ወንድሞቼ ሆይ፤ የጌታ ቃል
እንዲሮጥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ
እንደሚሆን እንዲከብር ስለ እኛ ፀልዩ፡፡" 2ተሰ 3፡1