ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

አይኖቻችንን በጌታ ኢየሱስ ላይ እናኑር!

የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላላው ደስታ መስቀሉን ታግሶ፤ የመስቀሉን ውርደት ንቆ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ 
ተቀምጧል፡፡

እንግዲህ ዝላችሁ ተስፋ እንዳትቆርጡ፤ ከኃጥያተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ የታገሰውን እርሱን አስቡ፡፡

(ዕብ 12, 2-3)

በህይወታችን ቅድሚያ ሊኖራቸው የሚገቡ ነገሮችን እኛ ካላስቀመጥን ሌሎች ሰዎችና በዙሪያችን ያሉ ሁኔታዎች ያስቀምጡልናል፡፡ ይህ ከሆነ ስጋትና ተስፋ መቁረጥ ይጋረጡብናል፡፡

1. ኢየሱስ ዓላማውን ያውቅ ነበር፤


ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ ይህ ሰው ደግሞ የአብርሃም ልጅ ስለሆነ፣ ዛሬ መዳን ወደዚህ ቤት መጥቷል፤ምክንያቱም የሰው ልጅ የመጣው የጠፉትን ሊፈልግና ሊያድን
ነው፡፡ (ሉቃ 19, 9-10)

እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው፡፡ በርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በርሱ የማያምን ግን
በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁኑኑ ተፈርዶበታል፡፡ (ዮሐ 3፤ 17-18)

በሉቃስ 15፤1-11 ላይ ስለጠፉት ነገሮች እንመለከታለን፡-

በጉ የጠፋው ተራ በሆነ ሁኔታ ነው፡፡

ሳንቲሙ የጠፋው በድንገት ነው፡፡

ልጁ ደግሞ የጠፋው ሆነ ብሎ ነው፡፡

መቅደም የሚገባውን ነገር ከማስቀመጣችን በፊት ዓላማችንን ማወቅ ይኖርብናል፡፡

2. ኢየሱስ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ሁኔታዎችን ያስቀመጠው በዓላማው ላይ ተመስርቶ ነው፡፡


ቅድሚያ አንድ፡

ከአባቱ ጋር ህብረት ማድረግ፤

ማለዳም ገና ጎህ ሳይቀድ፣ ኢየሱስ ተነስቶ ከቤት ወጣ፡፡ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራም ሄዶ ይጸልይ ጀመር፡፡ ስምዖንና ባልደረቦቹም ተከትለውት ይፈልጉት ጀመር፡፡
ባገኙትም ጊዜ "ሰው ሁሉ ይፈልግሃል" አሉት፡፡ ከዚህ ተነስተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ የመጣሁት ለዚሁ ነውና አላቸው፡፡
(ማር1፤35-38)

ቅድሚያ ሁለት:

የቅርቡ የሚሆኑትን ደቀመዛሙርት ማድረግ፤

ወደ ኢየሩሳሌም ለመውጣት በመንገድ ላይ ሳሉ፤ ኢየሱስ ፊት ፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ደቀመዛሙርቱ ተገረሙ፤ ሌሎች የተከተሉት ደግሞ ፈርተው ነበር፡፡ ደግሞም
አስራ ሁለቱን ከህዝቡ ለይቶ ምን እንደሚደርስበት ነገራቸው፡፡
(ማር 10፤32)

ቅድሚያ ሦስት:

የጠፉትን ማገልገል፤

የሰው ልጅ የመጣው የጠፉትን ሊፈልግና ሊያድን ነው፤ (ሉቃ19፤9)

3. ጌታ ኢየሱስ ተቀዳሚ ጉዳዮቹን ከሌሎች ሰዎች አጀንዳ ጠብቋል፡፡

ኢየሱስም ከዚያን ቀን ጀምሮ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ፣ በዚያም በሽማግሌዎች በካህናት አለቆችና በኦሪት ህግ መምህራን እጅ መከራን ይቀበልና ይገደል
ዘንድ፣ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳ ዘንድ እንደሚገባው ለደቀመዛሙርቱ ይገልጽለቸው ጀመር፡፡

ጴጥሮስም ኢየሱስን ወደ ጎን ሳብ አድርጎ "ጌታ ሆይ እንዲህ ያለው ነገር ፈጽሞ አይድረስብህ" እያለ ይገስጸው ጀመር፡፡
ኢየሱስም ወደ ጰጥሮስ ዘወር ብሎ "አንተ ሰይጣን ሂድ ከዚህ! የሰውን እንጂ የእግዚአብሔር ነገር በሐሳብህ ስለሌለ መሰናክል ሆነህብኛል" (ማቴ16፤21-23)
  1. ጌታ ኢየሱስ ዓላማውን አወቀ!
  2. ጌታ ኢየሱስ ተቀዳሚ ጉዳዮቹን በዓላማው መሰረት አስቀመጠ!
  3. ጌታ ኢየሱስ ተቀዳሚ ጉዳዮቹን ከሌሎች ሰዎች አጀንዳ ተከላከለ፡፡
አይኖቻችንን በጌታ ኢየሱስ ላይ እናድርግ!

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡