ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

አዳኙን ማወቅ፡ እርሱ ማነው?

ዮሐ 1፤1-3

ጌታ ኢየሱስ ማነው? ጌታ ኢየሱስ ላንተ/ላንቺ ማነው?

ጌታ ኢየሱስ በፍጥረቱ ምክንያት ጌታ ነው፤
(ዮሐ 1፤1-3, ኤፌ 3፤9, ቆላ1፤16, ዕብ 1፤ 1-2)

ታዋቂው ኢ-አማኝ ሮበርት ኤንገርሶል የተባለ ሰው ሄነሪ ዋርድ ቢቸርን በጎበኘበት ወቅት የሰማይ ከዋክብትን ስብስብ የሚያሳየውን ውብ ሉል አየ፡፡ በአትኩሮት ከተመለከተውም
በኋላ "ይህ እኔ ስፈልገው የነበረ ነው" አለ፡፡ ቢቸርም "ማን ሰራው?" "ማን ሰራው?" በማለትና በመገረም ደጋግሞ ተናገረ፡፡

እርሱም "ኮሎኔል ማንም አልሰራውም ግን እንዲሁ ሆነ፡፡" አለው፡፡ እርሱ የፍጥረት አካል አይደለም፤ ፈጣሪ እንጂ! እርሱ በገና በዓል ከሚታዩ በርካታ ስዕሎች በእጅጉ
የተለየ ነው፡፡ እርሱ ፈጣሪ ነው ስለሆነም ጌታ ነው፡፡ ያንተስ ጌታ ነውን?

ጌታ ኢየሱስ በሞቱና በትንሳኤው ምክንያት አዳኝ ነው!
(ዮሐ 1፤29, 3፤16-17)

ከሁሉ በበለጠ የሚያስፈልገን መረጃ ቢሆን፤ እግዚአብሔር አስተማሪ ይልክልን ነበር፤
ከሁሉ በበለጠ የሚያስፈልገን ቴክኖሎጂ ቢሆን፤ እግዚአብሔር ሳይንቲስት ይልክልን ነበር፤
ከሁሉ በበለጠ የሚያስፈልገን ገንዘብ ቢሆን፤ እግዚአብሔር ኢኮኖሚስት ይልክልን ነበር፤
ከሁሉ በበለጠ የሚያስፈልገን ደስታ ቢሆን፤ እግዚአብሔር አዝናኝ ሰው ይልክልን ነበር፤

ነገር ግን ከሁሉ በበለጠ የሚያስፈልገን የነበረው የኃጥያት ይቅርታ በመሆኑ አዳኝ ላከልን፡፡
የኃጥያተኞች እንኳ ጓደኛ ነበር፡፡ (ሳምራውያን - ዮሐ 4፤1-30, አመንዝራ ሴት ዮሐ 8፤1-11) እንደ ጌታ እርሱ የማዳን ኃይል አለው!
እርሱ ብቸኛው የዓለም አዳኝ ነው! (ዮሐ14፤6, የሐዋ.ሥራ 4, 12)

ኢየሱስ እንደ ፈራጅ ሊገለጥ በቅርብ ነው! (ዮሐ 5፤22, ሮሜ 2፤16, 14፤10; 2ጢሞ 4፤1)

አዳኛቸው ላልሆነ ፈራጅ ይሆንባቸዋል!
ጊዜው ከማለቁ በፊት ብንሰግድለት የተሻለ ይሆናል!

ጓደኛቸው እንዲሆንላቸው ለሚፈልጉት ጌታ ኢየሱስ ጓደኛ ነው፡፡

በህይወት በረከት ውስጥ (በቃና ሰርግ፤ ዮሐ 2፤1-11)
በመንፈሳዊ ሕይወቱ ግራ ለተጋባው (ኒቆድሞስ፤ ዮሐ 3፤1-21, ጴጥሮስ, ዮሐ 21፤15-17)
ለበሽተኛው (የአለቃው ልጅ, ዮሐ 4፤47-54, ቤተሳይዳ, John 5, 1-9, ዓይነስውሩ, ዮሐ 9፤6-7)
ለተራቡና ለድሆች (5.000, ዮሐ6፤10-13)

በሰውና በእግዚአብሔር መካካል ተፈጥሮአዊ የሐሳብ ርቀት ልንሰራ እንችላል፤ ነገር ግን ክፍተቱ በመሲሁ መሞላት ይኖርበታል!
እርሱ ጌታ፣ አዳኝ፣ ፈራጅ እና ጓደኛ ነው፡፡

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡