ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

እንደ ቤተሰብ ጌታን መገልገል

ልጆቻቸው ጌታን የማይከተሉ እጅግ በርካታ ቤተሰቦች አሉን፡፡ እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዲያገለግሉት ይፈልጋል፡፡

ከእግዚአብሔር የተሰጡ ትዕዛዛት
  • አባት (ኤፌ. 5፤23; 1 ጢሞ 3፤4-5).
አባት ቤተሰብን በሚከተሉት መንገዶች መምራት አለበት፡-
የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር (መመሪያ)፣
ከቤተሰብ ጋር በመጸለይ፣
በምሳሌያዊነት ህይወት በመመላለስ፣
ሚስቱንና ልጆቹን በመውደድ፣
ርህራሄንና ጽናትን በማሳየት፡፡

  • እናት (ምሳ 31፤ 25-28; ቲቶ 2፤3-5).
 እናት የቤት ውስጥ ኃላፊነቷን በሚከተሉት ሁኔታዎች በሚገባ መወጣት አለባት፡-
ለባሏና ለልጆቿ ሥጋዊና መንፈሳዊ ፍላጎት ጥንቃቄ በማድረግ፣
ቤቷን ከሁሉ በፊት ተቀዳሚ በማድረግ፤ (በጥሩ ስሜት),
የምትመች ረዳት ለሆነው ኃላፊነቷ ራሷን መስጠት፤

  • ልጆች፤ ምሳ 1፤8; ኤፌ 6፤1-2; ምሳ 23፤24-25).
ልጆች ወላጆቻቸውን በጌታ ማክበርና መታዘዝ ይኖርባቸዋል፤ 

የኢዮብ ልዩ ስብዕና (ኢዮ 1፤1-5)

ኢዮብ እግዚአብሔርን ፈራ፤ ከክፋትም ራቀ (ቁጥር 1) እንዲሁም እግዚአብሔርን አመለከ (ቁጥር 5) ፡፡ እንደ ጥሩ አባት በእግዚአብሔርና በልጆቹ ፊት ቅን
የሆነ ህይወትን ኖረ፡፡
ስለ ልጆቹ ሥጋዊና መንፈሳዊ ፍላጎት ተጠነቀቀ፡፡ ኃጥያታቸው ይቅር እንዲባልና በቅድስናም ይራመዱ ዘንድም ስለ እነርሱም ጸለየ፡፡

አብርሃም፡ እንደ መንፈሳዊ አባት ልዩ ስብዕና የነበረው ሰው፤ (ዘፍ18፤19)
አብርሃም የእግዚአብሔር ቃል ለእርሱና ለልጆቹ እውነት፣ ጥበብና በረከት እንደሆነ ሙሉ በሙሉ አመነ፡፡ ስለሆነም እርሱ እንዳደረገው በእግዚአብሔር መንገድ እንዲራመዱ
ልጆቹን አዘዘ፡፡
እንደ አባት መታዘዝን ለልጆቹ አስተማረ፡፡
እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዲያገለግሉት ይፈልጋል፡፡

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu

ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡