ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

እግዚአብሔርን ባለማስቀደም የምንፈጥረው ትርምስ

ኤር 2፤1-37

በመጽሐፈ ኤርሚያስ ውስጥ በጠቅላላው ሦስት ታሪኮች ተከስተዋል፡፡

የመጀመሪያው ታሪክ ወጣቱን ኤርሚያስን ይመለከታል፡፡ ኤርሚያስ ከበድ ላለ ሥራ በእግዚአብሔር የተመረጠ ሰው ነበር፡፡

ሁለተኛው ታሪክ በእግዚአብሔር የተመረጠውን የእስራኤልን ህዝብ ይመለከታል፡፡ ከብዙ ዓመታት እግዚአብሔር ካልነበረበት አመራርና ጣኦት አምልኮ በኋላ እግዚአብሔር
በቃ አለ፤ ለኤርሚያስም በባቢሎናውያን የሚወረሩበትን መጥፎ ዜና የመተንበይ ሥራን ሰጠው፡፡

ሦስተኛው ታሪክ ራሱን እግዚአብሔርን የሚመለከት ነው፡፡ ልጆቹ ወደ አመጽ መመለሳቸውን አይቶ ልቡ የተሰበረ አባት፡፡

እግዚአብሔር በህይወታችን የመጀመሪያ ካልሆነ ራሳችንን እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ይህም እግዚአብሔርን ባለመስቀደም የምትፈጥረው ትርምስ ነው፡፡
በእግዚአብሔር ለተመረጡት እስራኤላውያን ላይ የደረሰው ይኸው ነው፡፡

እነርሱም ከሌሎች ህዝቦችና ከሐሰት አማልክቶቻቸው ጋር መደባለቅ ጀመሩ፡፡ ከአይሁድ እምነት ውጭ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በጋብቻ ተጣመሩ፡፡ በመጀመሪያ የሚቆጣጠሩት
መስሎአቸው ነበር፤ግን ተቆጣጠራቸው፡፡

ማስጠንቀቂያ 1 - እግዚአብሔር ካስቀመጠው ደረጃ ውጭ የሆነን ነገር መከተል ስትጀምር ለአደጋ በሚያጋልጥህ አዳላጭ ቁልቁለት ላይ ነህ፡፡

ኤርሚያስ የእስራኤልን ውድቀት እጅግ ከበድ ባለ ሁኔታ አጠቃለለ፤

"ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፣ ከለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ " ( ኤር 2, 20ለ)

ለእስራኤል ሣሩ በአንድ በኩል እጅግ አረንጓዴ ሆኖ ታያት፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን በሌላኛው በኩል ጣኦቶቻቸውንና የሐሰት አምላክ የሆነውን በዓልን ማምለክ ጀመሩ፡፡ 
ሞሎክ ለተባለው የሐሰት አምላክ ልጆቻቸውን መስዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡ ቁጥር 28 ላይ አማልክቶቻቸው በከተሞቻቸው ቁጥር ልክ እንደነበሩ ይናገራል፡፡ በግብረ ሥጋዊ
ግንኙነት ልምምዳቸው ግብረ ገብ አልነበራቸውም፡፡ በመጀመሪያ ጉዳት ያለው አይመስልም፡፡ ትንሽ መርዛማ እባብም እንዲሁ ነው፡፡ ብዙም ሳይቆይ ይናደፋል፡፡ ብዙም ሳይቆይ
ሰውነትህን ሁሉ ያዳርስና ራስህን ትልቅ አደጋ ውስጥ ታገኘዋለህ፡፡ ከእግዚአብሔር ውጭ የሆነ ነገር መከተል በሚያዳልጥ አደገኛ ቁልቁለት ላይ መሆን ነው፡፡

መስጠንቀቂያ 2- እግዚአብሔርን የማይተሉ መሪዎችን መከተል ወደ ጥፋት መንገድ ይመራል፤

ይህ በርግጥ እስራኤል ያደረገችው ነው፡፡ ጻድቅ ሊሆን በሚገበው ሥፍራ ላይ እግዚአብሔርን የማይከተሉ ሰዎች ሲመሩ በቸልታ ታገሱአቸው፡፡

''እግዚአብሔር ወዴት አለ? ብለው ካህናቱ አልጠየቁም፤ ከህጉ ጋር የሚውሉት አላወቁኝም፤መሪዎቹ አመጹብኝ፤ ነቢያቱም በበዓል ስም ተነበዩ፤ ከንቱ ነገሮችን
ተከተሉ፡፡'' (ኤር 2፤8)


እስራኤል የሃይማኖት መሪዎቻቸው እግዚአብሔርን የማይፈልጉ ህዝቦች ነበሩ፡፡ ፋራጆቻቸው እግዚአብሔርን ወይም የስነምግባር ደረጃውን አላወቁም፡፡

ነገስታቱ በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ ከእግዚአብሔር መንግስት ይልቅ የራሳቸውን መንግስት ገነቡ፡፡ ሰባኪዎች ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የበዓልን ትምህርት ሰበኩ፡፡

እግዚአብሔርን የማይከተሉ መሪዎችን ስንከተል በእነርሱ የህይወት መርህ ለመዋጥ ብዙ ጊዜ አይፈጅብንም፡፡

ማስጠንቀቂያ 3 - እራስህን ከእግዚአብሔር ፊት ዘወር ማድረግ ራስህን ለውድቀት መዳረግ ነው፤

እስራኤላውያን መንገዳቸው ከእግዚአብሔር መንገድ የተሸለ እንደሆነ ወሰኑ፡፡

''ህዝቤ ሁለት ኃጥያት ፈጽመዋል፣ ህያው የውሃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተዋል፤ ውሃ መያዝ የማይችሉትን ቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶችን
ቆፍረዋል፡፡'' (ኤር 2፤13)


እስራኤል ኩልል ያለ ቀዝቃዛ የምንጭ ውሃ ወይም የረጋና የቆሸሸ ውሃ ከቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ሊኖራቸው ይችል ነበር፡፡ እስራኤላውያን የራሳቸውን መንገድ በመሄድ
የራሳቸውን ነገር አደረጉ፡፡

እራስህን ከእግዚአብሔር ፊት ዘወር ማድረግ ራስህን ለውድቀት መዳረግ ነው፤

ማስጠንቀቂያ 4 - ንስሃ መግባትን ቸል ማለት የልብ ድንዳኔን ያስከትላል፤

እስራኤላዉያን መሳሳታቸውን አምነው ከክፋታቸው ንስሃ መግባትን አልወደዱም፡፡ በመሆኑም ልባቸው ደነደነ፤ ባለመታዘዝም መኖርን ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር
ህዝቡን ከፊቱ ያስወግዳል፤ ምክንያቱም ወደርሱ ለመምጣት አልወደዱምና፡፡

"ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ" (ኤር 2፤27ለ)
የክፋታቸው ፍጻሜ ምን ነበር? ምዕራፍ 37 ላይ የባቢሎን መንግስት ገዢዎች እስራኤልን እንዲይዙ እግዚአብሔር ሲፈቅድ እንመለከታለን፡፡ የተቀጠረችውንም ከተማ
ከበቧት፤ በመጨረሻም ሰብረው ገቡ፡፡ ባለመታዘዙ ምክንያት የይሁዳ ንጉስ ተያዘ፡፡ ዓይኖቹ እያዩ ልጆቹ በፊቱ እንዲታረዱ ተደረገ፡፡ ዓይኖቹም ወጡ፤ እንዲሁም
ቀሪ ዘመኑንም በሰንሰለት ታስሮ በጨለማ እስር ቤት እንዲያሳልፍ ተደረገ፡፡ በኢየሩሳሌም የነበረው ቤተመንግስት ወደ አመድነት ሲቀየር ምርት ሁሉ ተቃጠለ፤
ቤተሰቦች ሁሉ ተወገዱ፡፡ አብዛኛው ህዝብ በምርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰዱ፤ በዚያም ባሪያ ሆኑ፡፡

ማስጠንቀቂያ 5 - ኃጥያት መዘዞች አሉት፤

አሁን ወይም የሚቀጥለው ሳምንት ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ኃጥያት መዘዞች አሉት፡፡

"እኔን መፍራት ቸል ስትይ፣ ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ አስቢ፣ እስቲ አስተውይ" (ኤር 2:19ለ).

ማናችንም ፍጹም ካለመሆናችን የተነሳ ሁላችንም እስከተወሰነ ድረስ መጽሐፍ ቅዱስ 'ኃጥያት' በሚለው የግብረግብ በሽታ እንጠቃለን፤ ስለሆነም እግዚአብሔር ደግሞ
የፍቅር አምላክ በመሆኑ ይሄን ያህል መጨነቅ የለብንም፤ጥቃቅን ስህተቶቻችንንም ያልፋቸዋል በማለት ለማሰብ እንፈልግ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ሁኔታው ከዚህ በእጅጉ
የጠነከረ ነው፡፡ ምንም እንኳ እግዚአብሔር እጅግ በጣም ቢወደንም ጽድቁና ፍትሃዊነቱ ከክፋት ጋር እንዳይኖር ያደርጉታል፡፡ ነቢዩ እንባቆምና ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳስቀመጡት
"ዓይኖችህ ክፉውን እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፤" (እን 1፤13)፣ "ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቶአችኋል፤ ኃጥያታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል" (ኢሳ 59፤2)

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡