ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

እግዚአብሔርን የማመስገን ደስታ

ሉቃ 12, 32

ሉቃስ እንደ ማቴዎስ፣ ጴጥሮስ፣ወይም ያዕቆብ ከኢየሱስ ጋር የመሄድና የማውራት እድልን አላገኘም፡፡ እርሱ ወንጌልን ሰምቶ እና ስለ እግዚአብሔር ልጅ በቃል ብቻ
የሰማውን በጽሑፍ በመዘገብ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ የወሰነ ሐኪም ነበረ፡፡ እርሱ ከአህዛብ ወገን የነበረ እና አይሁድ ያልሆኑት ሁሉ መረዳት በሚችሉበት ሁኔታ የወንጌልን
ታሪክ ስዕላዊ በሆነ መንገድ የጻፈ ሰው ነው፡፡

ለምንድነው ኢየሱስ "እናንተ አነስተኛ መንጋ የሆናችሁ አትፍሩ!" ያለው?

በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ቃሉን ለመስማት፤ለመመገብ፤ ወይም ፈውስን ለማግኘት ይመጡ ነበር፡፡ ነገር ግን ጥቂቶቹ ብቻ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ይገባሉ፡፡
እነርሱን ነው "አነስተኛ መንጋ" ብሎ የጠቀሰው፡፡

እግዚአብሔር ደስታን በኛና በልጆቻችን ያገኛል?
የመንግስቱ የሆኑት ይታመኑታል፡፡
እግዚአብሔር በእምነታችን ደስ ይለዋል፤ ዕብ11፤6: 'ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም!' ሮሜ 8፤8: '...በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን
ደስ ሊያሰኙት አይችሉም!' እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚፈልጉ ሁሉ ክርስቶስና የቅድስናው ውበት ይጠብቃሉ፡፡ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚፈልጉ ሁሉ
በቅድሚያ የእግዚአብሔርን መንግስትና ጽድቁን ይፈልጋሉ፡፡ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚፈልጉ ሁሉ እግዚአብሔርን ለመታመን ፈቃደኛ ናቸው፡፡
ከመንግስቱ የሆኑት ያመሰግኑታል፡፡
ዳዊት በመዝሙር 69፤30-31 "የእግዚአብሔርን ሥም በዝማሬ አወድሳለሁ፤በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፤ከበሬ ይልቅ፣ ቀንድና ጥፍር ካበቀለ እምቦሳ ይልቅ
ይህ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡" በሌላ አነጋገር እግዚአብሔርን የሚያስደስቱት ሊያመሰግኑት ፈቃደኛ የሆኑት ናቸው፡፡ እነርሱም ወደ አባታቸው ቤት ዝማሬ
ይዘው ይመጣሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ምስጋና ለመዘመር ፈቃደኛ ናቸው፡፡ እርሱን በዝማሬ ለማመስገን ፈቃደኛ መሆናችንና እግዚአብሔርን ከራሳችን ህይወት በላይ ከፍ
ስናደርገው ይህ እርሱን ከማንኛውም ተራና ልማዳዊ ሥርዓት ይልቅ ደስ ያሰኘዋል፡፡

ኢየሱስ ወደ መስቀል ከመሄዱ ጥቂት ቀደም ብሎ ለእግዚአብሔር ዘምሯል፡፡ መጽሐፍ እንደሚናገር "መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ"
(ማቴ 26, 30) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ህዝብ ለእግዚአብሔር መዝሙር የዘመሩበት ከ25 በላይ የሆኑ ስፍራዎች ተጠቅሰዋል፡፡ ጌታን ለማመስገን
ለሚወዱት እግዚአብሔር በምስጋናቸው ውስጥ ደስታን ይፈልጋል፡፡

ከመንግስቱ የሆኑት እርሱን ይሰብካሉ፤
እግዚአብሔርን ለማስደሰት የምንፈልግ ከሆነ ክርስቶስን መስበክ አለብን፡፡ ሰዎች መስማት የሚፈልጉትን ብቻ እየነገርናቸው ወንጌልን መስበክ አንችልም፡፡ (1 ቆሮ1፤21; ገላ1፤10)
መሻታችን ልክ እንደ ኢየሱስ መሆን አለበት፤"...እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና፤" (ዮሐ 8፤29, ሮሜ 15፤3) እኛ ለእርሱ ውድ መሆናችንን
ማወቅ ምንኛ ሥጦታ ነው! እኛን የእግዚአብሔር መንግስት ዜጎች ማድረጉ እርሱን ያስደስተዋል፡፡

የእግዚአብሔር መንግስት የምትታየው በኃይል እንጂ በቃል አይደለም፤ (1 ቆሮ 4, 20)
  1. የአቅርቦቱ ኃይል፡ እግዚአብሔር የእለት እንጀራችንን (ማቴ 6፤11), የህይወትን ውሃን (ዮሐ 4፤14), መጽናናትና እረፍትን (ማቴ 11፤28) ይሰጠናል፡፡
  2. የጥበቃው ኃይል፡ ይጠብቁን ዘንድ እግዚአብሔር መላዕክቱን ያዛል፤ (መዝ 91፤11-13)
  3. የተስፋዎቹ ኃይል: እግዚአብሔር ቃሉን ሰጠን፤ (መዝ 107፤20)

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡