ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

እግዚአብሔር በአብርሃም ህይወት ውስጥ፤

ዘፍ፤12፤8

መሰዊያዎችን መስራት፤


የአብርሃምን ህይወት ስናይ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን የጠበቀ ህብረት እንመለከታለን፤አብርሃም መሰዊያን እየሰራ የእግዚአብሔርን ሥም ይጠራ ነበር፡፡ በርግጥ የተነገረን
መሰዊያ እንደሚሰራ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ፤ ቤተመንግስትን ይሰራ እንደነበር አላነበብንም፡፡ በህይወቱ መጨረሻ ለባለቤቱ ሣራ መቃብር ሰርቷል፡፡ ነገር ግን በሄደበት ሥፍራ ሁሉ
መሰዊያ እየሰራ በህይወቱ የገጠመውን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ያዛምድ ነበር፡፡ አብርሃም ከሰራቸው መሰዊያዎች በስተጀርባ የህይወት ታሪኩን ዝርዝር ጉዳዮች ማውጣት
እንችላለን፡፡

አብርህም እግዚአብሔርን አመለከ፡፡ ከሁሉ የበለጠ ተግባሩ አምልኮ ነበር፡፡ ለምሳሌ በሚከተሉት ወቅቶች እግዚአብሔርን አምልኳል፤
 • ከግብጽ ሀገር ሲመለስ፤ (ዘፍ፤13፡2-4)
 • የተስፋይቱን ምድር ሥፋት ባየ ጊዜ፤ (ዘፍ13፤14-18)
 • እግዚአብሔር ተገልጦለት ስሙን ከአብራም ወደ አብርሃም በለወጠበት ጊዜ፤(ዘፍ 17፤3-5)
 • በቤርሳቤህ ከአቤሜሌክ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ፤ (Genesis 21, 33)
መሰዊያን መስራት ቀላል ሥራ አይደለም፡፡ ድንጋይና የድንጋይ ማጣበቂያ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን እጅግ አስቸጋሪ የነበረው መሰዊያ በሞሪያም ተራራ ላይ የተሰራው ነበር፡፡ 
ይህንን መሰዊያ ሲሰራ ምናልባት የተሰበረው የጀርባ አጥንቱ ሳይሆን ልቡ ነው፡፡ ይህንን መሰዊያ ይሰራ የነበረው ለገዛ ልጁ እንደነበር ያውቅ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ዓይን
ፊት አብርሃም ልጁን መስዋዕት አድርጎ አቅርቧል፡፡ በጉ በዚያ ሥፍራ የተገኘው በአጋጣሚ አይደለም፤ እግዚአብሔር አዘጋጅቶት ነበር እንጂ፡፡

የአብርሃም ስነመለኮት


በዘመኑ ከነበሩ ሰዎች ይልቅ አብርሃም እግዚአብሔርን ያውቅ ነበር፡፡ ታላላቅ እውነቶችን ሥለ ራሱ ለአብርሃም የገለጠለት ራሱ እግዚአብሔር ነበር፡፡ (ዘፍ18፤19) በወቅቱ
መጽሐፍ ቅዱስ አልነበረም፡፡ ስለ እግዚአብሔር ያለው ብቸኛው የመረጃ ምንጭ ራሱ እግዚአብሔር ነበር፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ለአብርሃም ገለጠ፡፡ አብርሃም ከእግዚአብሔር
ጋር ሲነጋገርና ስለ እግዚአብሔር ሲናገር የሚከተሉትን መግለጫዎች ተጠቅሟል፡፡
 • አዶናይ፤ (ጌታ፤የበላይ) - ዘፍ 15፤2
 • ያህዌ (ጌታ - እኔ ነኝ) - ዘፍ 15፤2
 • ኤልኤልዮን (ልዑል) - ዘፍ 14፤22
 • ኤልሻዳይ (ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር) - ዘፍ 17፤ 1
 • ኤልሮኢ (የሚያየኝ እግዚአብሔር) - ዘፍ 16፤12
 • ኤልኦላም (ዘላለማዊ እግዚአብሔር) - ዘፍ 21፤ 33
 • ያህዌ ይህዌ ይርዔ (የሚያዘጋጀው እግዚአብሔር)- ዘፍ 22፤14

አብርሃም መጽሐፍ ቅዱስ አልነበረውም፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ካላቸው ብዙዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ያውቅ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ የሄድንበት ሂደት
ህይወታችንን ይገልጻል፡፡ 'አምላክህን አሳየኝና እንዴት እንደምትኖር፤ እንዲሁም ዘላለማዊ ህይወትን እንዴት እንደምታሳልፍ እነግርሃለሁ!'

እግዚአብሔርን ማወቅ የሁሉ መሰረት ነው፤ ከርሱ ውጭ እውነተኛ ህይወትና አገልግሎት የለም፡፡

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡