ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

ከሲኦል በቀጥታ የተጸለየ ጸሎት

ሉቃስ 16፤19-31
ይሁዳ 22-23
1 ቆሮንቶስ16፤15

ተልዕኮዎች ምንድን ናቸው?


ተልዕኮዎች ሌሎች ወንጌልን እንዲሰሙ በሙሉ መሰጠት ማገልገል ማለት ነው!

ራሴን ለእግዚአብሔር በማስገዛትና የሚቻለኝን ሁሉ በማድረግ ከኔ ጋራ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ወደ ሲኦል ለመውረድ እንዳይወስኑ ፍላጎት አለኝን?

ተልዕኮዬ ምንድን ነው?
ተልኬያለሁን? እግዚአብሔር የሰጠኝን ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ተቀብያለሁን?
ለምንድን ነው ክርስቲያኖች በተልዕኮዎች ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን የሚገባቸው?

1. ሁለት ትልልቅ ጥያቄዎች
የሰው ጥያቄ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፡ 'እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?' (ዘፍ 4፤ 9)
ራሱን ፍጹም ለማድረግ ሲል ይህንን ጥያቄ የጠየቀው ቃየን ነበር፡፡
ሁለተኛው ትልቅ ጥያቄ: 'ባልንጀራዬ ማነው?' (ሉቃ 10፤ 29)
የህግ አዋቂው ባልንጀራው ማን እንደሆነ አያውቅም ነበር፡፡
እያንዳንዱ ክርስቲያን እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ ይበልጡኑ ጥያቆዎቹን መመለስ ይገባናል፡፡

2. ወደ ሲኦል ጉዞ - ሉቃስ 16፤19-31

ሲኦል መልእክተኞችን በመፈለግ በሚያለቅሱ ሰዎች የተሞላ ነው፡፡ ሲኦል እግዚአብሔርን የተውና ዘላለማዊ ህይወታቸውን ከእግዚአብሔር ውጭ የሚጋፈጡ ሰዎች
ስብስብ ነው፡፡ የመንፈሳዊ ሕይወትን እውነታ ያውቃሉ፤ ነገር ግን ሁሌም ያለ እግዚአብሔር ናቸው፡፡

ብዙ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ያነባሉ፤ እንዲሁም "እነሆኝ እኔን ላከኝ" በማለትም ይጸልያሉ፡፡ ይሁን እንጂ ላይ ላዩን በሆነው ህይወታቸው ከመርካት ውጭ
ለተልዕኮአቸው አንዳች ነገር አያደርጉም፡፡ ወደ ሲኦል ለሚሄዱትም ግድ አይላቸውም፡፡ በሐዋሪያት ሥራ ላይ የተጠቀሰው "የመቄዶናዊው ጥሪ" ለ21ኛው ክፍለ
ዘመን ክርስቲያኖች ተፈጻሚ ይሆናልን?

3. ስታቲስቲክስ

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በወንጌል ተልዕኮዎች ውስጥ የሚሳተፉ ክርስቲያኖች ቁጥር 3 % ብቻ ነው፡፡
ክርስቲያኖች ከወንጌል ተልዕኮ ይልቅ ለምግብ፣ ለውሾቻቸው እና ለድመቶቻቸው ብዙ ገንዘብ ያወጣሉ፡፡
እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች በየጊዜው ወደ ሲኦል እየወረዱ መሆናቸው እንግዳ ነገር ነውን?
አማካዩ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያናት እጅግ ቀላል የሆነውን ምስክርነት ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መስጠት አልቻሉም፡፡
በዓለም ከሁሉ የበለጠ ተነባቢ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች በሳመንት ከሦስት ምዕራፍ በላይ አያነቡም፡፡

4. ራዕይ
አንዳንድ ክርስቲያኖች ወደ መንግስተ ሰማያት በመሄዳቸው እጅግ ከመደሰታቸው የተነሳ ወደ ሲኦል የሚሄዱትን ረስተዋል፡፡ ይህ ራዕይ በአንድነት እንድንጸልይ፤
እንድንጾምና ሕይወታችንን ለጠፉት ሰዎች መዳን እንድንሰጥ ይረዳናል፡፡ ለጠፉ ሰዎች መዳን የሚሆነው ራዕይ ከክርስቲያን ቤቶች የሚጀምር ሆኖ ኪሳችንንና
የባንክ አካውንታችንን የሚጨምር መሆን ይኖርበታል፡፡

እኔ መሄድ የማልችል ከሆነ ሌላ ሰው መላክ ይኖርብኛል፡፡
ትልቁ አስፈላጊ ነገር ጸሎት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን የጠፋውን "የጸሎት ሰው የመሆን አስተሳሰብ" ያስፈልገናል፡፡
የወንጌል ተልዕኮዎች በህይወታችን ከሁሉ የበለጡ ተግዳሮቶቻችን ናቸው ወይስ ራሰችንን ባላደጉት አጥቢያዎቻችን ግድግዳ በስተጀርባ መደበቅን እንመርጥ ይሆን?

5. የዓለም ሁኔታ
በአሁኑ ጊዜ ካሉት 100 ሰዎች መካከል 66ቱ ሥለ ጌታ ኢየሱስ ፈጽሞውኑ አልሰሙም፡፡
70ቹ ነጭ ያልሆኑ ናቸው፡፡
57ቱ ኤስያውያን ናቸው፡፡
21ዱ አውሮፓውያን ናቸው፡፡
70ቹ ማንበብ አይችሉም፡፡
50ቹ ርቦአቸው ወደ መኝታ የሚሄዱ ናቸው፡፡
1ዱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በመሆኑ የሚኩራራ ነው፡፡
40ቹ ለወንጌል ክፍት የሆኑ ህጻናት ናቸው፡፡
6ቱ የዓለምን 50% ሀብት የያዙ ናቸው፡፡
3ቱ ለሲኦል በእጅጉ የቀረቡ ሲሆኑ ምናልባትም ዛሬም እንኳ፡፡
መንፈስ ቅዱስን ካልሰማን በስተቀር እዚህ ሁሉ መረጃዎች ትርጉም የላቸውም፡፡ እርሱ በኛ ውስጥ መስራትን ይፈልጋል፡፡

6. የእግዚአብሔር ዓላማ ለክርስቲያኖች

ብዙ መጸለይና ለወንጌል ተልእኮ ግድ መሰኘት፤
ጥቂት ጥያቄዎች መጠየቅ ይጠበቅብናል፤
እኔ ንቁ ተሳታፊ እንደሆንሁ ሁሉም አባላት ተሳታፊ ቢሆኑ ቤተክርስቲያናችን ምን መልክ ይኖራት ነበር?
እኔ የምሰጠውን ያህል ሁሉም አባላት ቢሰጡ ቤተክርስቲያናችን ምን መልክ ይኖራት ነበር?
እኔ የምጸልየውን ያህል ሁሉም አባላት ቢጸልዩ ቤተክርስቲያናችን ምን መልክ ይኖራት ነበር?
የበለጠ መሥራት እችላለሁን?
የበለጠ መስጠት እችላለሁን?
የበለጠ መጸለይ እችላለሁን?
ስለ ጌታ ኢየሱስ የመሰከርክላቸውንና ብቸኛውን አዳኝ አመልክተሃቸው በመንግስተ ሰማያት የምታገኛቸውን ሰዎች አስብ፤
አንተ ካልሆንክ ታዲያ ማን?
እዚህ ባይሆን ታዲያ የት?
አሁን ካልሆነ ታዲያ መቼ?

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡