የሐዋሪያው ጳውሎስ ግብዣ
ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ (በኤፌሶን 5 መሰረት) በቅድስና ህይወት እንድንኖር ሊያበረታታን ከዚህ ቀጥሎ ወዳሉት ቦታዎች ይጋብዘናል፤
1. ቤተመቅደስ (ኤፌ. 5፤1-7)
ሐዋሪያው በቤተመቅደስ ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ ያደረገልንን መስዋዕት ያስታውሰናል፤ ሐጥያት መጥፎና በእግዚአብሔር ፊት የሚገማ ሽታ ያለው ነገር ነው፤ (ኢሳ 3፤ 24)
በፍቅር የምንጓዝ ከሆነ ህይወታችን ህያው መስዋዕት (ሮሜ 12, 1-2; ፊል 2, 17) እና ለጌታም መልካም መዓዛ ያለው ሽታ (ዮሐ 12፤1-8) ይሆናል፡፡
2. ሜዳ (ኤፌ 5፤ 8-14)
ከዚያም ሐዋሪያው ጳውሎስ ፍሬ ሊያሳየን ወደ ሜዳ ይሄድና በብርሃን መመላለስ መንፈሳዊ ፍሬን እንደሚያፈራ ያስታውሰናል፤ (ገላ 5፤ 22-23)
በብርሃን ብንመላለስ ከጨላማ ጋር ህብረት አይኖረንም፤ (2 ቆሮ 6፤14-18)
3. የንግድ ሥፍራ (ኤፌ 5፤ 15-17)
ከዚያም ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ንግድ ሥፍራ ይወስደንና መልካም አጋጣሚዎችን እንዴት መጠቀም እንዳለበት የሚያውቅ ጥሩ ነጋዴ እንድንሆን ያደፋፍረናል፤
በጥበብ የምንመላለስ ከሆነ ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀማለን፤
4. የግብዣ አዳራሽ (ኤፌ 5፤18-21)
ከዚያም በመንፈስ እንዴት መመላላስ እንዳለብን (ገላ 5, 16-26) ወደ ምንማርበትን የግብዣ አዳራሽ (ኤፌ 5, 18-19) ሐዋሪያውን እንከተላለን ፡፡
በመንፈስ የምንመላለስ ከሆነ ደስተኞት፤አመስጋኞች እና እርስ በርሳችን ትሁታን እንሆናለን፡፡
5. ቤት (ኤፌ 5፤ 22-33)
የመጨረሻው የሐዋሪያው ጳውሎስ ጉብኝት ጋብቻን እንደ ክርስቶስና ቤተክርስቲያን ግንኙነት የሳለበትን ቤት ነው፡፡ ኢየሱስ ወደደን ስለዚህም ሞተልን፡፡ ዛሬም
ይወደናል ደግሞም ይጠነቀቅልናል፡፡ ይህ የጠበቀ ግንኙነት በማሕልየ መሓልይ ዘሰለሞን ውስጥ የተገለጸ ሲሆን ዛሬም ሕይወታቸውን ለሚሰጡት ሁሉ እውን ይሆናል፡፡
ለጌታ ኢየሱስ የተሰጠን ስንሆን ህይወታችን ለሌሎች በረከት ይሆናል፡፡
ዶ/ር ቼስላው ባሳራ
This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
; www.proword.eu