ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

የመልዕክቶች ማውጫ

ሁለን ትተው ተከተሉት

ሉቃ 5፤1-11

ዕቅድ ቁጥር 1
እግዚአብሔር ሊያስተምርህ ዝግጁ ነው!

አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ጠይቅ አጠገብ ሳለ ህዝቡ በዙሪያው እያጨናነቁት የሚያስተምረውን የእግዚአብሔር ቃል ይሰሙ ነበር፤ (ሉቃ 5፤1)

ትምህርት ቁጥር 1
እኔ ለማዳመጥ ዝግጁ ከሆንኩ እግዚአብሔር ሊያስተምረኝ ዝግጁ ነው!
ዕቅድ ቁጥር 2
እግዚአብሔር ኃይሉን ሊያሳይህ ዝግጁ ነው!

በዚያን ጊዜ ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ዳርቻ ቆመው አየ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ወርደው መረባቸውን ያጥቡ ነበር፡፡ ከጀልባዎቹ መካከል የስምዖን
ወደ ነበረችው ገብቶ፣ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤ ከዚያም ጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር፤ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን፣
"ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ በልና ዓሣ ለማጥመድ መረባችሁን ጣሉ" አለው፡፡ ስምዖንም መልሶ "መምህር ሆይ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም፤
አንተ ካልክ ግን መረቦቹን እጥላለሁ" አለው፡፡ እንደዚያም ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፤ መረባቸውም ይበጣጠስ ጀመር፡፡ በሌላ ጀልባ የነበሩት ባልንጀሮቻው
መጥተው እንዲያግዟቸው በምልክት ጠሯቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱን ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፣ ጀልባዎቹም መስጠም ጀመሩ፡፡ (ሉቃ 5፤2-7).

Read more: ሁለን ትተው ተከተሉት

   

ለማገልገል ድነናል!

የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይኖራል፡፡ የሚያገለግለኝም ቢኖር አባቴ ያከብረዋል፡፡ (ዮሐ12፤26)

አገልጋይ ጌታውን ይከተላል፤ የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ...

ጌታ ኢየሱስ አገልጋይ ጌታውን እንደሚከተል በግልጽ ተናግሯል! አለቃው ምን ማድረግ እንዳለበት የመንገር መብት በጭራሽ የአገልጋዩ አይደለም፡፡ ክርስቶስን መከተል
ማለት በርሱ መንፈስ መመራት፤በርሱ ጥበብ ምርጫዎቸን ማድረግ፤ለርሱ መኖር፤እርሱ እንድናደርግ የሚፈልገውን ሁሉ ማድረግ ማለት ነው!

አገልጋይ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን በግሪክ ዶሎስ (ከጌታው ጨርሶ የማይለይ ባሪያ) የሚለውን ያመለክታል፡፡ አንዳንዴ ዴአኮኖስ (ዲያቆን ወይም አገልጋይ)
የሚለውን ያመለክታል፡፡ ዶሎስ እና ዴአኮኖስ ተመሳሳይ ቃላት በመሆናቸው ይሄ ትክክል ነው፡፡ ሁለቱም ቃላት በራሱ ፈቃድ እንደወደደ የማይኖረውን፤ ነገር ግን
በዋጋ የተገዛ የጌታው ንብረት የሆነን ሰው ያመለክታሉ፡፡ እኛ የጌታን ፈቃድ ለማገልገል በዋጋ የተገዛን ነን፡፡

አገልጋዮቹ እንዲሰሩት ጌታ ኢየሱስ ያዘጋጀው ሥራ ምንድነው? ምንም እንኳ ዋጋ የሚያስከፍልና ክብርን የሚነካ ቢሆንም አብረዋቸው ለሚያገለግሉት እንደባሪያ
እንዲሆኑና እነርሱን ለማገዝ ሲባል ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፈቃደኛ በመሆን እንዴት ሊያገለግሉት እንደሚገባ ነግሮአቸዋል፡፡

Read more: ለማገልገል ድነናል!

   

በሸክላ ሰሪው ቤት ውስጥ

ኤር18፤ 1-11

የጽሑፉ ታሪካዊ ትርጉም


ሸክላ ሰሪው ግልጽ እቅድ እንደነበረው ኤርሚያስ አስተዋለ፡፡ ሸክላ ሰሪው ለሸክላው ልዩ ቅርጽ ለመስጠት የተካኑ እጆቹንና የተለያዩ መሳሪያዎችን ተጠቀመ፡፡
ሸክላው የሚያገለግለው በሸክላ ሰሪው አዕምሮ ውስጥ የነበረን ሐሳብ ነው፡፡
  • ሸክላ ሰሪው ጭቃውን መረጠ እንጂ ጭቃው ሸክላ ሰሪውን አልመረጠም፤
  • ሸክላ ሰሪው የወደደውን ጭቃ መረጠ፡፡
  • ሸክላ ሰሪው ለሸክላው ቅርጽ ለመስጠት ጉልበቱን ተጠቅሟል፡፡
ትልቁ ሸክላ ሰሪ ለእያንዳንዳችን ዕቅድ አለው፡፡ (ኤር 1፤18; 2፤11)
  • ኤርሚያስ እግዚአብሔርን እንደ ሸክላ ሰሪ እና እስራኤልን እንደ ጭቃ ተመለከተ፡፡
  • እግዚአብሔር ለእስራኤል እቅድ ነበረው፡፡
  • እግዚአብሔር የተለያዩ በረከቶችን በመላክ ልዩ የሆነ ቅርጽን ሰጣት፤
  • እግዚአብሔር ፍርድን በመስጠት ልዩ የሆነ ቅርጽን ሰጣት፤

Read more: በሸክላ ሰሪው ቤት ውስጥ

   

በተስፋ መቁረጥ ወቅት የእግዚአብሔር ማበረታታት ያስፈልገናል፤

ዕብ 10፤23-35 - የእግዚአብሔር ህዝቦች ሁሉ መበረታታትን ይፈልጋሉ፤

1. ይስሃቅ ማበረታታት አስፈልጎት ነበር፤ 'በረሃብ ሀገር እባርክሃለሁ!'
"እግዚአብሔር ለይስሃቅ ተገልጦ እንዲህ አለ፤እኔ በምነግርህ ምድር ተቀመጥ እንጂ፣ ወደ ግብጽ አትውረድ፤ ለጥቂት ጊዜ እዚሁ ተቀመጥ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤
እባርክሃለሁ፤ ይህንን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘርህ በመስጠት ለአባትህ አብርሃም በመሃላ ገባሁትን ቃል አጸናለሁ" (ዘፍ 26፤2-3)

(ዘፍ 26፤12-13).

ይስሃቅ ይኖር በነበረበት ሀገር የምግብ እጥረት ባጋጠመው ጊዜ እግዚአብሔር ወደ ግብጽ እንዳይወርድ ነገር ግን ባለበት ሀገር እንዲቆይ ተናገረው፡፡ እግዚአብሔርም
በዚህ አገር እንደሚባርከው ለይስሃቅ ቃል ገባለት፤

እግዚአብሔርም ይስሃቅን አበለጸገው፡፡ በዘራም ጊዜ መቶ እጥፍ ምርትን ሰበሰበ፡፡ ይስሃቅ እጅግ ባለጠጋ እስኪሆን ድረስ ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረለት ሄደ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ትግል፣ዕጥረትና ጉዳት ባጋጠመን ሥፍራ እግዚአብሔር ሊባርከን ይችላል፡፡ ምናልባት ህመምና ስጋት ካገኘን ሥፍራ ለማምለጥ እንዳዳ ይሆናል፡፡
እግዚአብሔር ብርቱ ኃይሉን ስለ እኛ በመግለጥ እጥረትና ሥጋት ባጋጠመን ሥፍራ ሊባርከን ቃል ገብቷል፡፡

Read more: በተስፋ መቁረጥ ወቅት የእግዚአብሔር ማበረታታት ያስፈልገናል፤

   

በቶሎ እመጣለሁ! ጌታ ኢየሱስ

ራዕ 3፤ 11-12

1. 'እነሆ ቶሎ እመጣለሁ!'

1.1. የጌታ ኢየሱስ ወደ ኤፌሶን፤ ጴርጋሞን እና ሰርመኔስ መምጣት ለፍርድ ሲሆን ወደ ፍላድልፍያ የመጣው ግን የመከራቸውን ዘመን ለመዝጋት ነበር፡፡

1.2. 'እነሆ በቶሎ እመጣለሁ!' ለጨቋኞች ማስጠንቀቂያ ሲሆን ለጭቁኖች ደግሞ ማበረታቻ ነው፡፡
 
1.3. ክርስቲያኖች ለጌታ ኢየሱስ ምጽዓት ሁሌም ዝግጁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ (ራዕ፤3፤3) የኢየሱስ ክርስቶስ በድንገት መምጣት በታማኝነት እያገለገሉ ለመጠበቅ አነሳሽ ነው፡፡

2. ቤተ መቅደሱ


በራዕ 3፡10 የተጠቀሰው የመጠበቅ ሰዓት በዚህ ሥፍራ የተገለጸው ከጌታ ኢየሱስ ለቤተክርስቲያኑ መመለስ ጋር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ የሚዛመደው አንድም ከሚሊኒየሙ
መንግስት አሊያም ከአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ጋር ነው፡፡ እውነተኛ አማኝ በእግዚአብሔር ፊት የአገልግሎትና የክብር ሥፍራ ይሰጠዋል፡፡

Read more: በቶሎ እመጣለሁ! ጌታ ኢየሱስ

   

Page 1 of 13

<< Start < Prev 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 Next > End >>
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡