ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

የእግዚአብሔር ቃል ለእኔ ምን ትርጉም አለው?

ከእኔ የሰማኸውን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር፤ የጤናማ ትምህርት ምሳሌ አድርገህ ያዝ፤ (2 ጢሞ 1፤13)

1. የጤናማ ትምህርት ምሳሌ
በ2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡13 ውስጥ 'ምሳሌ' የሚለው አገላለጽ 'የአንድ መሓንድስ ንድፍ' ማለት ነው፡፡ ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ጀምሮ ግልጽ የእምነት መግለጫ ነበር፡፡ እርሱም
ሁሉም ትምህርቶች የሚመዘኑበት መለኪያ ነበር፡፡ ጢሞቴዎስ የዚህን መግለጫ ይዘት እንዳይለውጥ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው፡፡ ከለወጠው አብሮአቸው የሚሰራውን የእነዚያን
አስተማሪዎች ትምህርት የሚመዝንበት ምንም ነገር አይኖረውም፡፡ እኛ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያለን ሐዋሪያው ጳውሎስ በ1ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያስተመረውን
አጥብቀን መያዝ ይኖርብናል፡፡ በጥንቷ ቤተክርስቲያን 'አንቲኖሜኒዛም' የሚባል ፍልስፍና ተስፋፍቶ ነበር፡፡ ትምህርቱም 'ከህግ በታች አይደለንም' የሚል ነበር፡፡ ይህ አስተሳሰብ
ዛሬም ቢሆን የሞተ አይደለም፡፡ እኛ ከጸጋ በታች እንጂ ከህግ በታች አይደለንም የሚሉ አንዳንዶች አሉ፡፡ ይህ አስተምህሮ አዲስ ኪዳን የፍቅር ደብዳቤዎች ስብስብ እንጂ
የህግ ዝርዝር አይደለም ይላል፡፡ አንዳንዶች 'ምሳሌያዊ የስነ-መለኮት ትምህርት' የሚሉትን አይቀበሉም፡፡ የጤናማ ትምህርት ምሳሌ የሚለው ሀረግ እንድንኖርበት የተገባን
ህግ መኖሩን አያሳይም ወይ?(1 ቆሮ 9፤ 21; ገላ 6፤2)

2. አጽንተህ ያዝ!
ለምዕተ አመታት የእግዚአብሔር ሥራ በፈተናቸው ወቅት ጸንተው በቆሙ ህዝቦች ሲሰራ ነበር፡፡ ቢያመቻምቹ ይቀላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ጸንተው ቆሙ፡፡ ሐዋሪያው
ጳውሎስ ካላመቻመቹት መካከል አንዱ ነበር፡፡ ወደ ህይወቱ ፍጻሜ አካባቢ በጌታ ወንድሙ ለሆነው ወጣቱን ጢሞቴዎስን ሊያበረታታው ፈለገ፡፡ ፡፡ በ1 ቲሞቴዎስ 1፤11
እግዚአብሔር የተከማቸ መንፈሳዊ እውቀት ለሐዋሪያው ጳውሎስ እንደሰጠና እርሱም ይህንኑ ለጢሞቴዎስ እንዳስተላለፈ ደግሞ እናነባለን (1ጢሞ 6፤20) ፡፡
እንደ 2 ጢሞ 1፤13 ጸንቶ መቆምና ውድ የሆነውን የተከማቸ እውነት ጠብቆ ለሌሎች ማስተላለፍ የጢሞቴዎስ ኃላፊነት ሆነ፡፡ (1 ጢሞ 2፤2)

3. ከእኔ የሰማኸው
መንፈስ ቅዱስ የእውነት መንፈስ እንደሆነ እናምናለን፡፡ እርሱም እውነትን ለጢሞቴዎስ አደራ ሰጠው፡፡ እኛ አንድ መንፈስ ቅዱስ እና ከእርሱም የሚመጣ አንድ
እውነት ብቻ አለን፡፡ ስለሆነም በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ እውነቶች አናምንም፡፡ እግዚአብሔር እውነቱን ያስተምረን ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ለመላክ ወሰነ፡፡
ከመንፈስ አገልግሎት ውጭ ከሆንን በጨለማ ውስጥ ነን፡፡ ያለእርሱ የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት አንችልም፡፡ ሁልጊዜም በእርሱ ትምህርት ሥር መሆን ይገባናል
(ዮሐ 16፤13) ፡፡ እርሱ እውነትን እንድንጠብቅና ለሌሎችም እንድናካፍል ያስችለናል፡፡

4. እምነትና ፍቅር
የጢሞቲዎስ ትምህርት መቅረብ ያለበት 'በእምነትና በፍቅር' መሆኑን ማስተዋል ይኖርብናል፡፡ እርሱም እውነትን በፍቅር መናገር ይኖርበታል፤ ምክንያቱን ይኼ
የእግዚአብሔር አሰራር ነውና፡፡ እግዚአብሔር እውነትን ያለፍቅር አይናገርም፡፡ ኤፌ 4፤15 'እውነትን በፍቅር እየተናገርን' ይላል፡፡ እምነትን ለመጠበቅ ባለን
መሻት ተከራካሪ መሆን እንዴት ቀላል ይሆናል! እውነትን ከመካፈል ይልቅ ስለ እውነት የራሱን ትርጓሜ በመስጠት ችግር የሚፈጥረውን መተተኛ ማጥመድስ
እንዴት ቀላል ይሆናል! አጭር የጽድቅና የክርስትና ህይወት አስተምህሮ መግለጫ፡ 'እምነት ጌቶች ያደርገናል፤ፍቅር ደግሞ አገልጋዮች ያደርገናል' የሚል ነው፡፡
እምነት ምንጊዜም ወደ ጌታ ኢየሱስ የሚያመለክትና በእርሱ ላይ የጸና መሆን ይኖርበታል፡፡ እምነት (በግልጽ አነጋገር) በቤተክርስቲያን ወይም በሌላ ዓይነት ጸጋ
በማመን ጨርሶዉኑ አይገኝም፡፡

5. በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ
የሰማይ በረከቶች ሁሉ ምንጭ የሚገኘው በክርሰቶስ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ እምነት ነፍስ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነውን የደህንነት ህብረት ከሚቤዣት ከኢየሱስ ክርስቶስ
ጋር የምትፈጥርበት መሳሪያ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ 'ሕግ በመጠበቅ የሚገኝ የራሴ ጽድቅ ኖሮኝ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚመጣ፤ ከእምነት
በሆነ ጽድቅ በእርሱ ዘንድ እንድንገኝ ነው፤' (ፊል 3፤9)

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡