ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

የወንጌል ተልዕኮ ለልጆች ለምን ያስፈልገናል

ሐዋሪያው ጳውሎስ በሮሜ 1፤16 ላይ እንደተናገረው ወንጌል 'ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡' የመጨረሻው የጌታ ኢየሱስ ትዕዛዝ 'ወንጌልንም 
ለፍጥረት ሁሉ ሥበኩ' የሚል ነበር፡፡ (ማር 16፤15)

1. የወንጌል ተልዕኮ ለልጆች ያስፈለገበት የመጀመሪያውና ዋንኛው ምክንያት በጌታ ኢየሱስ ትዕዛዝ ውስጥ ይገኛል፡፡ ክርስቲያኖች የእርሱን ትዕዛዝ ማስወገድ ወይም ወደ
ጎን መተው አይችሉም፡፡ ጌታ ኢየሱስ ልጆች ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ይወዳል (ማር10፤14; ማቴ 18፤14) ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የወንጌል ሥርጭት ማለት ሰዉን
ሁሉ ልጆችን ጨምሮ መድረስ ነው፡፡

2. ልጆች መንፈሳዊ ፍላጎት አላቸው፡፡ ያለጌታ ኢየሱስ በመንፈስ ሙታን ናቸው፡፡ የሐጥያት ችግር አለባቸው፤ ስለሆነም በጌታ ኢየሱስ መታመን ይኖርባቸዋል፡፡

3. ልጆች በቀላል እምነታቸው ለወንጌል ምላሽ መስጠት ይችላሉ፡፡ ፓት ቨርቫል የተባለ 'የልጆች አገልግሎት ጸሐፊ እና የዓለም አቀፍ የልጆች አገልግሎት ጥምረትአማካሪ'
እንደገለጸው 'ዛሬ ካሉት ክርስቲያኖች መካከል ከ75-85% ያህሉ ስለ እምነታቸው ውሳኔ ያደረጉት ከ15 ዕድሜ በታች ባሉበት ወቅት ነው፡፡'

4. ልጆች ለወንጌል በጣም ክፍት ናቸው፡፡ እንደ ባርና ጥናት ክርስቶስን የመቀበል እድል ከወጣቶችና ከጎልማሶች ይልቅ በልጆች መካከል በጣም ይልቃል፡፡ በ 5 እና 13
እድሜ ክልል ውስጥ ባሉት ልጆች መካከል ክርስቶስን የመቀበል እድል 32% ነው፡፡ በ 14 እና 18 እድሜ ክልል ባሉት ልጆች መካከል ደግሞ ቁጥሩ በ 4% ዝቅ ሲል፤
በቀሩት የህይወት ዘመናት ቁጥሩ ወደ 6% ብቻ ከፍ ይላል፡፡

5. ልጆች ረጅም የወደፊት ህይወት አላቸው፡፡ ልጆችን በወንጌል መድረስ በመጪው ዘመን ላይ መስራት ነው፡፡ የዓለም ህዝብ በአሁኑ ጊዜ ከ6.000.000.000.
በላይ ደርሷል፡፡ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ቢያንስ አንድ ሦስተኛው ልጆች ሲሆኑ እነርሱም የቤተክርስቲያንና የሀገር ተስፋዎች ናቸው፡፡ የዳነ ልጅ የዳነ ህይወት ደግሞ ነው፡፡፡

6. ልጆች ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ለማዳን የእግዚአብሔር መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ቤተሰቦች፤ወላጆችና ቅድመ ወላጆች በዳኑ ልጆች ቀላል ምስክርነት ሊድኑ ይችላሉ፡፡
ጓደኞችም እንዲሁ ለክርስቶስ ሊማረኩ ይችላሉ፡፡ በዚህ መንገድ ልጆች ለአጥቢያ ቤተ ክርቲያን በረከት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

7. በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ልጆች ታላቅ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ ማርቲን ሉተር እንዲህ ሲል ተናግሯል፡- 'የእግዚአብሔር መንግስት በኃይል ትመጣ ዘንድ በልጆች
መጀመር አለብን፤ገና በመታቀፊያቸው ውስጥ ካሉበት ጊዜ ጀምሮ ልናስተምራቸው ይገባል፡፡' ቻርለስ ስፐርጂን እንዲህ ሲል ጽፏል፡- 'ህጻናት ወንጌል ያስፈልጋቸዋል፡፡
ሙሉ ወንጌል፤ ንጹህ ወንጌል ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ከእግዚአብሔር መንፈስ ከተማሩ በእድሜ እንደ በሰሉ ሰዎች የመቀበል አቅም አላቸው፡፡' የአይ.ኤን.ሲ.ኤም.
የቀድሞ ፕሬዚዳንት የሚከተለውን ጠቅሷል፡-ዲን ስቶን 'የልጆች አገልግሎት የቤተክርስቲያን ትልቁ የአገልግሎት ስልት ነው፤...በአጥቢያ ቤተክርስቲያን የአገልግሎት
ልቀት የሚጀምረው ከጨቅላ ህጻናት ተነስቶ ወደ ላይ የሚቀጥል ነው፡፡'

8. ልጆች በመንፈስ ቅድስ የተሰጡ ሰዎችን ይፈልጋሉ፡፡ እነዚያ ሰዎች ህጻናትን መስተማርና በወንጌል መድረስ ይችላሉ፡፡ (ሮሜ 1፤16).

9. ልጆችን በወንጌል በመድረስ አገልግሎት ውስጥ ብንሳትፍ እግዚአብሔርን እናከብራለን፡፡ቤተሰብ ወይም አስተማሪ ብቻ ሳይሆኑ የሁሉም ክርስቲያን ትልቁ መሻት
እግዚአብሔርን ማክበር ነው፡፡ ልጆች ሲድኑ እና ለጌታ ኢየሱስ ሲኖሩና ሲያድጉ ለእርሱ ክብርን ያመጣሉ! ይኼ እግዚአብሔር የሚጠብቀው ፍሬ ነው! ልጆችን በወንጌል
መድረስ እግዚአብሔርን ማክበር ነው፡፡

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡