ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

የዛሬ ልጆች ምን ዓይነት መልዕክት ይፈልጋሉ?

1. ስለ እግዚአብሔር መስማት ያስፈልጋቸዋል፤ 
እግዚአብሔር የደህንነት ምንጭ ነው፡፡ ልጆች እግዚአብሔር ማን እንደሆና ምን እንደሰራ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
ልጆች ስለ እግዚአብሔር ግልጽ ሥዕል ሳይኖራቸው ስለኃጥያት ያለባቸውን ኃላፊነት በጭራሽ መረዳት አይችሉም፡፡

የሚከተሉትንም የምናስተምረው ለዚሁ ነው፤
 • እግዚአብሔር ፈጠረህ፤ (የሐዋ. ሥራ17፤23-29)፤ በእርሱ ፊት ኃላፊነት አለብህ፡፡
 • እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ በኩል ተናግሮሃል፤ (1 ቆሮ15፤ 3-4): እርሱን የመስማት ኃላፊነት አለብህ፡፡
 • እግዚአብሔር ቅዱስና ጻድቅ ነው፤ (የሐዋ. ሥራ 17፤31)፤ ይዳኝሃል፡፡
 • እግዚአብሔር መልካም ነው፤ ይወድሃል፡፡ (ዮሐ 3፤16): እርሱ ደህንነትን ቀላል አድርጎልሃል፡፡

2. ስለ ኃጥያት መስማት ያስፈልጋቸዋል፤
ስለ ኃጥያት ማስተማር የደህንነትን አስፈላጊነት ያሳያል፡፡ ኃጥያትና መዘዙን በሚገባና አስረግጦ ማብራራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ነው የሚከተሉትን የምናስተምረው፡-
 • ኃጥያትህ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡ (መዝ 51, 4).
 • በተፈጥሮ ኃጥያተኛ ነህ፤ (ኤፌ 2፤3) እንዲሁም በተግባር፤ (ሮሜ 3፤23).
 • ስለኃጥያህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቅጣት ይገባሃል፡፡ (ሮሜ1፤18)

3. ስለኢየሱስ ክርስቶስ መስማት ያስፈልጋቸዋል፤
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ብቸኛው የደህንነት መንገድ ለልጆች ያሳያል፡፡ ልጆች ኢየሱስ ክርስቶስ ማን እንደሆነና ምን እንዳደረገ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
ለዚህም ነው የሚከተሉትን የምናስተምረው፡-
 • ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው አዳኝ የሆነው እግዚአብሔር ወልድ ነው፡፡ (Acts 9፤20)
 • እርሱ ስለኃጥያትህ ሞቷል፡፡ (የሐዋ. ሥራ 2፤23.36.38)
 • ከሞት ተነስቶልሃል፤(የሐዋ. ሥራ 2, 24-32)
 • ወደ ሰማይ ተመልሶ ሄዶልሃል፤(የሐዋ. ሥራ 2፤23-32)

4. ስለ ንስሃና ስለ እምነት መስማት ያስፈልጋቸዋል፤
ህጻናትን ወደ ክርስቶስ መጥራት የወንጌል ዋንኛው ከፍል ነው፡፡ (ዮሐ 6፤37; ዮሐ1፤12)

ለዚህም ነው የሚከተሉትን የምናስተምረው፤
 • ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ እንድትመጣ ይጋብዝሃል፡፡ ( ማቴ 11፤28)
 • ከኃጥያትህ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ይኖርብሃል፤ (የሐዋ.ሥራ 2፤38; 20፤21)
 • ጌታ ኢየሱስን መታመንና ሙሉ በሙሉ ልትገዛለት ይገባል፡፡ (የሐዋ.ሥራ 16፤31; 20፤21).
ንስሃ መግባትና እምነት ለክርስቶስ ጥሪ ሙሉ ምላሽ ማለትም የአዕምሮ፤የልብና የፈቃድ፤መስጠትን ያካትታሉ፤ (ሮሜ 6፤17)				

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡