ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

ድህረ ዘመናዊ ልጆችን መድረስ

(1 ዜና12፤32)

1. ልጆቻችን ስለሚኖሩበት ዘመን ምን የተለየ ነገር አለ?
ድህረ ዘመናዊ ትውልድ ማንኛውም አመለካከት ካለንበት አቅጣጫ አኳያ ይወሰናል በማለት ያስባል፡፡ እስከተወሰነ ደረጃ ድረስ ሐሳቡ እውነትነት አለው፡፡ አብዛኛውን
ጊዜ ነገሮችን ከራሳችን አቅጣጫ ብቻ ለማየት እንፈልጋለን፡፡ ድህረ ዘመናዊ ትውልድ ስለ ዘመናዊነት ምክንያታዊ ተዓማኒነት እና ስለ ቀደመው እውቀትና እምነት መኖር
ጤናማ የሆነ ጥርጣሬ አለው፡፡

2. ሦስት የአስተሳሰብ ዘይቤዎች:

2.1 እምነትን ማእከል ያደረገ፤ /Theocentrism/
2.2 ዘመናዊነት /Modernism/
2.3 ድህረ ዘመናዊነት /Postmodernism/

3. ወንጌልን ድህረ ዘመናዊ ለሆነ ትውልድ ማቅረብ፤

ስለ ወንጌል ሥርጭት ያለንን አስተሳሰብ ማስፋት ይኖርብናል፤
ድህረ ዘመናዊያን ባህላዊውን ያለማስረጃ የሆነ አቀራረብ የሚቀበሉ አይደሉም፡፡ ስለ ህይወትና እውነታ በድህረ ዘመናዊነት አስተሳሰብ ላይ የተመሰረቱ ጥያቄዎች አሏቸው፡፡
ድህረ ዘመናዊነትን መመለስ የክርስቶስን ትምህርቶች በማስተዋውቅ ሂደት ውስጥ ድርሻ ሊኖረው ይገባል፡፡ የማንኛውም አገልግሎት ዓላማ ሰዎች ከጠላትነት ወደ እግዚአብሔር
ፍቅር እንዲመለሱ ማገዝ ነው፡፡ (ዘዳ. 6፤5)

ከድህረ ዘመናዊው ትወልድ ጋር ያለንን የጋራ መሰረት ማድነቅ ይኖርብናል፡፡

ከድህረ ዘመናዊነት ትውልድ ጋር የምንጋራቸውን እጅግ በርካታ መሰረቶችን መረዳት ይኖርብናል፡፡ ከታሪካዊው የክርስትና ዓለም አመለካከት ጋር የሚዛመዱ በርካታ እምነቶችና
እሴቶች በድህረ ዘመናዊነት ባህል ውስጥ በከፊል ወይም በሙሉ ይገኛሉ፡፡ እነርሱም ግንኙነት ልንፈጥርበት የሚያስችለን የጋራ መሰረት ይሆኑልናል፡፡

ለምሳሌ፡-
የምዕራባውያን ባህል እያደገ አይደለም፤
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አማኝ ክርስቲያኖች የሰው ልጆች እንከን የለሽ በሆነ ዓለም ውስጥ እየኖሩ እንዳሉ ጨርሶ አምነን አናውቅም፡፡ ወንጌላውያን በዚህ ጽንሰ
ሐሳብ ላይ ከድህረ ዘመናዊው ትውልድ ጋር ይስማማሉ፡፡ ቴክኖሎጂ ወደ ፍጹም አለም የማይወስደን ከሆነ ወዴት እየሄድን ነው ብለን ሰዎችን መጠየቅ እንችላለን፡፡
ዘመናዊነት ቀና አስተሳሰብ ያለው ሲሆን ድህረ ዘመናዊነት ግን እንደዚህ አይደለም፡፡

ስለ ዘረኝነትነና ፍትሃዊነት ግንዛቤ ድህረ ዘመናዊው ትውልድ ስለ ዘር እና ስለ ጾታ ግድ ይለዋል፡፡ እኛም እነዚህ ጉዳዮች እንዲዳሰሱ እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን
የፍትሃዊነትና የእኩልነት መመዘኛዎቹ ምን መሆን አለባቸው?

ስለ ተፈጥሮ ያለን ግንዛቤ
ድህረ ዘመናዊው ትውልድ የአየር መዛባትን በመቃወም በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ ክርስቲያኖችም ስለ ፕላኔታችን ከምን ጊዜውም በበለጠ ጠንካራ የባለአደራነት ስሜት
ሊያድርብን ይገባል፡፡ ስለሆነም ንጹህና የተሻለ ዓለም ለማየት ያላቸውን ፍላጎት ልንጋራ ይገባል፡፡

በስነ ጥበብ ፈጠራ ላይ ያለ ትኩረት
ሐዋሪያው ጳውሎስ በአሪዮስፋጎስ ከነቢያቶቻቸው ሳይሆን ከአካባቢው ባህላዊ ጽሑፍ ሲጠቅስ እንመለከታለን፡፡ (ሐዋ 17) ምንም እንኳ እነርሱ ባያውቁትም ክርስቲያኖች
የእግዚአብሔርን መልክ የሚያሳይ መልእክት እንዴት ከባህል ውስጥ ሊወጣ እንደሚችል በማስተዋል ፈጠራን መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡

ግንኙነት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፤

ድህረ ዘመናዊው ትውልድ ቢሆንለት ለእውነት ታላቅ ዋጋ የሚሰጥ ማህበረሰብ ነው፡፡ በሥላሴ እምነታችን፤ በሰዎች የሕይወት ልምምድ ውስጥ ያሉ ግንኙነቶችን ደግሞ እናያለን፡፡

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡