ይህ ድረ ገጽ ላንተ በረከት ሆኖአልን?Results

ጌታ ኢየሱስ ማነው? ምንስ አደረገ?

(እንደ ራዕ 3፤7-9)	

የፍላድልፍያ ከተማ
በፈላድልፍያ የነበረችው ቤተክርስቲያን በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ከሌሎቹ ሰባት ቤተክርስቲያናት የተሻለ ነገር ለእግዚአብሔር ሠርታለች፡፡ ቤተክርስቲያኒቷ ለተልዕኮዋ
ታማኝ ነበረች፡፡ ለጌታም የቀረበ ህይወት ነበራት፤ሲያወግዛትም አንመለከትም፤ኃጥያቷን እንኳ አልገለጠም፡፡ ተገዳሮቷ ከፊቷ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ በከፈተላት በር ትሄድ ይሆንን?

ጌታ ኢየሱስ - ጸሐፊው
በራዕ 3፤7-13 ጌታ ኢየሱስ ራሱን ያስተዋወቀው መልዕክቱን የሚቀበሉት ወገኖች ሊረዱት በሚችሉበት ቋንቋ ነበር፡፡

1. እርሱ ቅዱስ ነው፤ (ራዕ 3፤7)
ጌታ ኢየሱስ በሥነምግባሩ እንከን እና ስህተት ወይም ነቀፋ የሌለበት ነው፡፡ በባህሪው እንከን የለሽ ነው፡፡ ቅድስና የእግዚአብሔር ልዩ መለያው ነው፡፡ 'ቅዱሱ' የሚለው
መጠሪያ በአይሁዳውያን እጅግ የታወቀው የእግዚአብሔር ስያሜ ነው፡፡ በኢሳይያስ 43፤15 ላይ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ 'እኔ እግዚአብሔር የእናንተ ቅዱስ፣የእስራኤል
ፈጣሪ ንጉሳችሁ ነኝ፤' የኢየሱስ ክርስቶስን ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ቅድስና ማየት ይገባናል፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡ ስለሆነም ኃጥያትን ይጸየፋል፡፡ የማያምኑ ሰዎች
የኃጥያት ችግራቸውን እንዲፈታላቸው ሊፈቅዱለት ይገባል፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡ ስለሆነም አማኞች እንዲሁ ቅዱስ ሊሆኑ ይገባል፡፡

2. እርሱ እውነት ነው፤(ራዕ 3፤7)
ጌታ ኢየሱስ ከሁሉ ነገር በስተጀርባ ያለ፤ ፍጹም ታማኝ እና የማይናወጥ ነው፡፡
እርሱም ስለ ራሱ እንዲህ አለ፡- "እውነተኛ የሆነው!" በመጀመሪያው ቋንቋ (አናቴኖስ) ማለት ህያው፤ እውነተኛ፤ እና ሐቀኛ የሆነ ማለት ነው፡፡ በጌታ ኢየሱስ ውስጥ
ህያውነትን እናያለን፡፡ ስለ እርሱ ስናስብ ፍጹም ከሆነ እውነት ጋር እንገናኛለን፡፡ ኢየሱስ ህያው ነው፡፡ እውነተኛ ነው ስንልም ማንኛውም እርሱ የተናገረው ቃል እውነተኛ
የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እና ማንኛውም እርሱ የገባው ተስፋ ሁሉ እንደሚጠበቅ ነው፡፡ ስለሆነም በእርሱ ላይ የምንደገፍ ከሆነ ለደህንነት ልንታመነው እንችላለን፡፡
እንደ አማኞች ጌታ ኢየሱስ የነገረን
ሁሉ እውነት መሆኑን መረዳት ይኖርብናል፡፡ እርሱ 'በተከፈተ በር እድል' የሚገናኘን ከሆነ ይህ ማለት እርሱ በከፈተልን በር መሄድና እና እንድንሰራው የወደደውን ነገር መስራት
ይኖርብናል ማለት ነው፡፡

3. የዳዊትን መክፈቻ በእጁ ይዟል፤ (ራዕ 3፤7)
መክፈቻዎቹ ሥልጣንን ያመለክታሉ፡፡ ጌታ ኢየሱስ 'የዳዊትን መክፈቻ' ይዟል፡፡ የዳዊት መክፈቻ የተጠቀሰበት ሌላው ብቸኛ ሥፍራ የኢሳይያስ መጽሐፍ (ኢሳ 22፤20-23)
ነው፡፡በንጉስ ሕዝቅያስ ዘመነ መንግስት ኤልያቄም የዳዊት ቤት መክፈቻ ተሰጥቶት ነበረ፡፡ ይህ መክፈቻ የይሁዳ ንጉስ የከበሩ ሀብቶች የሚገኙበትን ቤት ይከፍት ነበር፡፡ ኤልያቄም
ማን ወደ ውስጥ መግባት እንዳለበት፤ማን ወደ ውጭ መውጣት እንዳለበት እንዲሁም ወደ ንጉስ ዳዊት መግባት የተገባውን ሁሉ ይቆጣጠር ነበር፡፡ ከንጉሱ ቀጥሎ ያለ ምክትል
ነበር፡፡ እርሱ በሮቹን የሚከፍትና የሚዘጋ ሰው ነበር፡፡

4. ወደዳቸው፤ (ራዕ 3፤9)
ጌታ ኢየሱስ የፍላድልፍያን ከባድ ሁኔታ ተገንዝቧል፡፡ ጌታ ኢየሱስ እጅግ ምርጥ የሆነው እንዲሆንላቸው ወደደ (ዮሐ 16, 27) ፡፡ በፍላድልፍያ የሚኖሩት (ወንድማዊ
ፍቅር) የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫ ነበር፡፡ በቅድሚያ የእግዚአብሔርን ፍቅር ሳይቀበሉ እውነተኛ ወንድማዊ ፍቅር ሊኖር አይችልም፡፡ የማያምኑ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ስለ
ፍቅር መሞቱን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ እርሱ ኃጥያተኞችን ከፍቅሩ የተነሳ የማዳን ፍላጎት አለው (ዮሐ 3፤16; ሮሜ5፤8) ፡፡

ዶ/ር ቼስላው ባሳራ

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ; www.proword.eu
ጀምስ  ኤን. ስፐርጂን የሚከተለውን ጽፏል፡

"ሥራ ባንተ ምርጫ ነው፤ አገልግሎት የጌታ ጥሪ ነው፤ በስራ ክፍያን ትጠብቃለህ፤ በአገልግሎት እንድትሰጥ ይጠበቅብሃል፤ በስራ አንድን ነገር ለመቀበል ሌላ ነገር ትሰጣለህ፤ በአገልግሎት አስቀድሞ የተሰጠህን መልሰህ ትሰጣለህ፤ ሥራ
በአንተ ችሎታ ላይ ይመሰረታል፤ አገልግሎት ግን ለእግዚአብሔር በመገኘት ላይ ይመሰረታል፤ በአግባቡ የተሰራ ሥራ ምስጋናን ያስገኛል፤ በአግባቡ የተሰጠ አገልግሎት ለኢየሱስ ክብርን ያመጣል፡፡"

የዚህ አገልግሎት ዓላማ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርን ለማምጣት ነው፡፡

በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያሉ መልእክቶችን ይዘት ሳይለውጡና ለአብ የሆነውን አገልግሎታችን በመጥቀስ መገልበጥ እና መጠቀም ይቻላል፡፡ እንዲሁም ለአድማጮችህና ለአንባቢዎችህ ይህንን መልእክት ያገኘህበት ድረ ገጽ፡
www.proword.eu እንድትነግራቸው ተጋብዘሃል፡፡ እርሱም ቃሉን ማወጅ ፤ ልጆችን በወንጌል የመድረስ አለም ዓቀፍ የመጽሀፍ ቅዱስ አገልግሎት ነው፡፡